ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ነገሮች
1 ተጫራቾች የዘመኑ ግብር የከፈሉና የታደሰ የ2011 ዓ/ም ንግድ ፍቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
2 ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ በታወቀ በባንከ የተረጋገጠ ቼክ ወይም ስፒኦ ብር 10,000 ማስያዝ አለበት፤
3 ተጫራቾች ከ 13/07/2011ዓ/ም ጅምሮ ሰራተኛ ማህበር ካሸር ክፍል 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በመምጣት የማይመለስ ብር /ሃምሳ ኣምስት/ 50.00 በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከገዙ በኃላ ለሽያጭ የተዘጋጁ ዕቃዎችን አዋሽ የእህል መጋዘን አጠገብ በሚገኘዉ መጋዝን ዉስጥ ለጨረታ የተዘጋጀዉ ዕቃዎችን በኣካል ቦታዉ ድረስ በመሄድ በስራ ሰዓት ማየት ይጠበቅባቸዋል።
4 ተጫራቾች ዕቃዎቹን የሚገዙበት የጠቅላላ ዋጋ ያለ ቫቱ 15% በማስቀመጥ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ አዘጋጅተዉ ሙሉ አድራሻቸዉ በመግለፅ ሰራተኛ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 ያዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን 13/07/2011 ዓ/ም እስከ 19/07/2011 ዓ/ም ከቀኑ 8:00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ከዚህ በኃላ የሚቀርበዉ ማንኛዉም ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
5 ጨረታዉ ፍላጎት ያላቸዉ ተጫረቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት 19/07/2011 ዓ/ም ከቀኑ 8:15 በሰሜን ሪጅን ኢትዩ ቴሌኮም 5ኛ ፎቅ የሚገኘዉ የስብሳባ አዳራሽ ይከፈታል።
6 አሸናፊዉ ተጫራቾች ላሸነፈዉ ዋጋ 15% ቫትን ጨምሮ ገቢ ካደረገ በኃላ በአምስት /5/ የስራ ቀናት ዉስጥ ለጨረታ ተለይቶ የተዘጋጁ አሮጌ ጣዉላ : የጣዉላ ሳጥን : ኬብሉ ና ብረቱ የተፈታ ድራም ብቻ በስራ ሰዓት ማንሳት ኣለባቸው። ሆኖም ግን በጊዜ ገደብ ካላነሱ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ስፒኦ ተደርጎ ሪጅኑ የራሱን አማራጭ ይወስዳል።
7 ዕቃዎቹ በሙሉ ካልሆነ በከፊል መጫረት ኣይችሉም።
8 መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፤
9 አንድ ተጫራች ባቀረበዉ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም
ስልክ ቁጥር 0344-418626
Backs