ትራንስ ኢትዪጰያ ኃ/የተ/የግል ማህበር በመቐሌ ዋና መስሪያ ቤት ግቢ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶች በጨረታ ኣወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
  • Posted Date: ሓሙስ ታኅሣሥ 25, 2011 (over 6 years ago)
  • Closing Date: ሮብ ጥር 15, 2011 08:00 Afternoon (closed)
  • Bid Bond:5000.00
  • location: መቐለ
  • Bid Document Price:50.00
  • Bid Opening Date: ሮብ ጥር 15, 2011 08:30 Afternoon
  • Other Sale/ Used Items Sale/
  • Print
  • Pdf

1 ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00 (ሃምሳ ብር) በመክፈል ከታህሳስ 24/2011ዓ/ም ጀምሮ መቐለ ከሚገኘው ጽ/ቤት ግዥ፣ንብረት ቁጥጥር መምርያ ቢሮ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።

2 ተጨራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ 5000.00 ኣምስት ሺ ብር በሲፒአ መልክ በትራንስ ኢትዩጰያ ኃ/የተ/የግል ማህበር ስም ማስያዝ አለባቸዉ።

3 ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ ጨምሮ መሆኑ እና አለመሆኑን መግልፅ አለባቸዉ። ያስገቡት ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ ጨምሮ መሆኑን ወይም ቲኦቲ ካልተገለፀ ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዳላካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።

4 ተጫራቾች የጨረታ ዋጋቸዉ በፖስታ አሽገዉ በግዢ ንብረት አቅርቦትና ቁጥጥር መምሪያ በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ እስከ 15/05/2011 ዓ/ም 8:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸዉ።

5 ጨረታዉ 15/05/2011ዓ/ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በትንሾዋ ኣደራሽ ይከፈታል ።

6 የጨረታ አሸናፊ ገንዘብ ገቢ በማድረግ ጨረታዉ ከሸነፈበት ቀን ጅምሮ በ5 ቀናት ዉስጥ በራሱ ማጓጓዣ በመጠቀም ያሸነፈውን ጠቅላላ (በሙሉ) ማንሳት ኣለበት።

7 የጨረታው ኣሸናፊ ያሸነፋቸው ዕቃዎች ገንዘቡን ገቢ ኣድርጎ ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ካላነሳ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ለኩባንያቸን ገቢ ሆኖ በጨረታው ቀጥሎ ላለው ኣሸናፊ ይሰጣል።

8 የዕቃው መጠን ግዜ ከተጠቀሰው መጠን ሊጨምር ወይም ሊቀንስ እንደሚችል ተጫራቾች ኣስቀድመው መገንዘብ ኣለባቸው።

9 ኩባንያዉ ጨረታዉ በምሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ

ተጨማሪ ማብራርያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0344-408205/0344-404070 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ

Backs
Tender Category