ራያ ዩኒቨርሲቲ የጽዳት መሳሪያ እቃዎች በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
  • Posted Date: ቀዳሜ ጥቅምት 10, 2011 (over 6 years ago)
  • Closing Date: ሰኞ ጥቅምት 26, 2011 03:00 Morning (closed)
  • Bid Bond: 50,000.00
  • location: ማይጨዉ
  • Bid Document Price:100.00
  • Bid Opening Date: ሰኞ ጥቅምት 26, 2011 03:30 Morning
  • Cleaning & Janitorial Equipments/
  • Print
  • Pdf

ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ የጨረታ ቁጥር ራዩ 003/2011 ዓ.ም

ራያ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተመለከተውን ምድብ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።

ምድብ

የዕቃው/አገልግሎት አይነት

የጨ/ማ ዋስትና መጠን

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አይነት

ጨረታው የሚዘጋበት ቀን

ጨረታው የሚከፈትበት ቀን

ምድብ 1

የጽዳት መሳሪያ እቃዎች

50,000

ሲፒኦ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር መቅረብ አለበት

በ16ኛው ቀን

3፡00 ሰዓት

በ16ኛው ቀን

3፡30 ሰዓት

  1. የ2010/11 ዓ.ም በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውም የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን ጊዜው ያላለፈበት የተሰጠ የምስክር ወረቀት (ታክስ ክሊራንስ) የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ከፋይነት የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ በፌዴራል መንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳዳር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የአቅራቢዎች ዝርዝር ወይም ሰፕላይ ሊስት ውስጥ በዌብ ሳይታቸው በዕቃ (አገልግሎት) አቅራቢነት የተመዘገቡ መሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ለተከታታይ 16 ቀናት በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ አድሚን ህንፃ ቁጥር 5 ግዥ ቡድን 2ኛ ፎቅ ዘወትር በስራ ሰዓት በመቅረብ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የፋይናንሻል ሰነዳቸው አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ የጨረታ ሣጥን ከመዘጋቱ በፊት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት በ16ኛው ቀን እስከ 3፡00 ሰዓት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ከላይ በተራ ቁጥር 2 በተጠቀሰው አድራሻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  4. ጨረታው በ16ኛው ልክ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ አድሚን ህንፃ ቁጥር 5 ግዥ ቡድን 2ኛ ፎቅ ይከፈታል። ነገር ግን በ16ኛው ቀን ሃይማኖታዊ ወይም መንግሥታዊ በዓል ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
  5. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ይሆናል።
  6. የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ መዘዣ ቼክ ወይም የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት በፖስታ ታሽጎ ለብቻ ማህተምና ፊርማ ተደርጎ ማቅረብ ይኖርበታል።
  7. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎቹን በራሱ ትራንስፖርት እስከ ራያ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ የማቅረብ ግዴታ አለበት።
  8. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈውን ዕቃ ውል ከማሰሩ በፊት ሳምፕል ማቅረብ ይኖርበታል።
  9. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- WWW.rayu.edu.et ወይም በስልክ ቁጥር 034 877 05 01/034 247 93 54 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።

የራያ ዩኒቨርሲቲ ግዥና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት

Backs
Tender Category