ፋብሪካችን ሞሓ የለስላሳ መጠጦች ኢንዳስትሪ አክስዩን ማህበር መቐለ ፋብሪካ ለፋብሪካ ኣገልግሎት የሚውል (calcium Hypo Chlorite) የተባለ የኬምካል ኣይነት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መምርያ ኣክብራችሁ መወዳደር የምትችሉ ተጫራቾች ሁሉ መጫኝ የምትችሉ መሆኑ በኣክብሮት እንገልፃለን።
  • Posted Date: ሓሙስ ጥቅምት 8, 2011 (over 6 years ago)
  • Closing Date: ኣርብ ጥቅምት 16, 2011 08:15 Afternoon (closed)
  • Bid Bond:2%
  • location: መቐለ
  • Bid Document Price:30.00
  • Bid Opening Date: ኣርብ ጥቅምት 16, 2011 08:30 Afternoon
  • Chemicals and Reagents/
  • Print
  • Pdf

1 ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ : የኣቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት: የቫት ተመዝጋቢ መሆኑ የሚረጋግጥ ሰርተፊኬት እና ቲን ምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል

2 ተጫራቾች ለጨረታዉ ማስከበሪያ የጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 2% የገንዘብ ክፍያ ማዘዣ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል

3 ተጫራቾች የሚቀርቡትን ዋጋ ቫት ያካተተ ሙሆኑን እና አለመሆኑን በግልፅ መቀመጥ ይኖርበታል ይህ ካልሆነ ግን ዋጋዉ ቫትን ያካተተ መሆኑ ታሳቢ ይደረጋል

4 የጨረታዉ ዝርዝር ሰነድ ከድርጅቱ ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 15 ድረስ በመመጣት መዉሰድ እና የማይመለስ ብር 30.00 በመክፈል ሰነድ መዉሰድ ይችላሉ

5 በጨረታ ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት ኣይኖረዉም

6 ተጫረቾች ዋጋቸዉ በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህን ጨረታ ከወጣበት ግዜ ጀምሮ እስክ ከ 16/02/2011 ዓ/ም በስራ ቀንና ሰዓት ኣክሱም ሆቴል ፊት ለፊት ከሚገኘዉ ዋና ቢሮኣችን ድረስ በመምጣት ለዚሁ ተብሎ በተዘገጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ እና የሰነዱ ማሽግያ ፖስታ ተጫራቾች ህጋዊ ማህተምና እና ፊርማ መኖር ይኖርበታል

7 የጨረታ ሳጥኑ 16/02/2011 ዓ/ም ከቀኑ 8:15 የሚታሸግ ሲሆን ከዚሁ ሰዓት ባኃላ የጨረታ ሰነድ የሚመጣ ተቀባይነት ኣይኖረዉም

8 ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት/ ባልተገኙበትም 16/02/2011 ዓ/ም ከቀኑ ልክ 8:30 በፋብሪካዉ የግዥና ክምችት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 19 ወስጥ ይከፈታል

9 ተጫራቾች በዘህ ጨረታ ላይ ያሸነፈቸዉን የእቃ አይነቶች ማሸነፋቸዉ እንደተነገራቸዉ በ7 ቀናት ወስጥ እቃዎችን የማስረከብ ግዴታ ይኖርባቸዋል።ይህ ሳይሆን ሲቀር ግን ያስያዘዉ የዉል የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ካለ ምንም ቅድመ ሆኔታ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል

10 ማንኛዉም ተጫራች ጨረታዉ ከተከፈተ ባኃላ ጨረታዉን መሰረዝ ኣይችልም

11 ስርዝ ድልዝ የሆነ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረዉም

12 ድርጅቱ የተሻላ አማራጭ ካገኘ በማንኛዉም ግዜ ጨረታዉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ

Backs
Tender Category