የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐለ ዲስትሪክት 1ኛ ለአቶ አታኸልቲ ሐጎስ ገ/ዝጊ እንዲሁም 2ኛ. ለገነት ጠብታ አግሮ ፕሮሰሲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለሰጠው ብድር አመላለስ በዋስትና የያዘውን ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/11 በተሰጠው ስልጣን መሠረት በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል::
የተበዳሪው/ መያዣ ሰጪው ሰም | የመያዣ ንብረቱ አድራሻ | ለጨረታ የቀረበ ንብረት ዓይነትና ዝርዝር | የቦታው ስፋት በካ/ሜ | የጨረታው መነሻ ዋጋ /በብር | የጨረታው ደረጃ | ጨረታየሚከናወንበት ቀን እና ሰዓት |
---|
አቶ አታኽልቲ ሓጎስ ገ/ዝጊ | በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን አከሱም ከተማ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር 7299/ድ/2016 የሆነ | የሆቴል ድርጅት ህንፃዎች እና የሆቴል መገልገያ ቁሳቁሶች | 4552.74 | ብር 27,806,388.86 /ሀያ ሰባት ሚሊዮን ስምንት መቶ ስድስት ሺህ ሦስት መቶ ሰማንያ ስምንት ብር ከ86 ሣንቲም/ | የመጀመርያ ጨረታ | ጥር 27 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00-6:00 |
የገነት ጠብታ አግሮ ፕሮሰሲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የቲማቲም ማቀናበርያ ፋብሪካ ህንፃ እና ማሸነሪዎች | በትግራይ ክልል አድዋ ከተማ ደበርቺ ቀበሌ ህንፃ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር 2969/2005 የሆነ ማሽነሪዎች እና አይሱዙ ተሽከርካሪ ሞዴል NPR71H26 | የቲማቲም ማቀነባበርያ ፋብሪካ | 3500ካ/ሜ | ብር 10,558,627.77/አስር ሚሊዮን አምስት መቶ ሃምሳ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ ሃያ ሰባት ብር ከ77 ሣንቲም | የመጀመርያ ጨረታ | ጥር 28 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 4:00–6:00 |
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የመያዣ ንብረት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመግዛት ንብረቱን የሚገዙበትን ዋጋ፣ ስምና አድራሻቸውን በመጥቀስ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐለ ዲስትሪክት የአታኽልቲ ሓጎስ ገ/ዝጊ ሆቴል ድርጅት እስከ ጥር 26 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡50 ሰዓት ድረስ እንዲሁም የገነት ጠብታ አግሮ ፕሮሰሲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የቲማቲም ማቀነባበሪያ ፋብሪካ እስከ ጥር 27 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡50 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4 በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰንጠረዡ በተመለከተው ቀንና ሰዓት በኢትዮጵያ ልማት ባንከ መቐለ ዲስትሪክት ፅሕፈት ቤት ይካሄዳል፡፡
- በጨረታው የተሻለ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ማሸነፉን የሚገልፅ ደብዳቤ ከባንኩ ሲደርሰው አሸናፊ ይሆናል።
- የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው ተሽከርካሪ እና ማሽነሪዎችን በተመለከተ ገዢው የቀረጥ ነፃ መብት ሊኖረው ይገባል ወይም በንብረቶቹ ላይ በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥና ታክስ ለመክፈል ይገደዳል፡፡
- ባንኩ ለሽያጭ የቀረቡትን ንብረቶች የሚሸጠው ከተቻለ ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ሲሆን አሸናፊው በባንኩ ብድር ፖሊሲና የአሰራር ስርዓት መሠረት አስፈላጊውን መስፈርቶች ካሟላና ፕሮጀክቱን የሚያስቀጥል ከሆነ ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት መጠየቅ ይችላል፡፡
- በጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ናቸው፡፡
- የንብረቱ ስመ ንብረት ለገዢው እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል። ገዢው ጉዳዩን ተከታትሎ ያስፈፅማል።
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች የሽያጩን 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ከፍያዎች፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ይከፍላል።
- በጨረታው ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት በኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐለ ዲስትሪከት በሚገኘው ሎን ሪቨው ዲቨዥን በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 09-14-70-33-62/09-42-70–79–20 (034 440 7439 ፣ 034 441 9016) ደውሎ ማግኘት ይቻላል፡፡ ንብረቱን መጐብኘት የሚፈልግ ከዲቪዥኖቹ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጐብኘት ይቻላል፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐለ ዲስትሪክት
Backs