የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር -1/2017ዓ/ም
በትግራይ ክልል ትግራይ መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ ግዥና ንብረት ኣሰተዳደር ለ2017 በጀትዓመት የብሮድካስትና ተዛማጅ እቃዎች በሃገር ኣቀፍ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ኣለባቸው።
➢ የ2017ዓ/ም ህድሳት የተደረገለት ንግድ ፍቃድ፣ የኣቅራቢነት ምዝገባ ሰርቲፊኬት ቲን ምዝገባ ወረቀትን የመስከረም ወር 2017 የቫት ዲክላሬሽን ማቅረብ ኣለባቸው
➢ መስፈርቶቹን የሚያሟሉ ሁሉም ተጫራቾች | ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15(አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 400.00 ( ኣራት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነድ ከትግራይ መገነኛ ብዙኃን ኤጀንሲ ግዥና ንብረት ኣሰተዳደር ቢሮ ቁጥር 105 ከቀን 24/03/2017 ዓ/ም እስከ 08/04/25017 ዓ/ም ከቀኑ 11:30 ድረስ በስራ ሰአት ሰነዶችን መግዛት ትችላላቹ ።
➢ ጨረታው የሚዘጋበት የመጨረሻ ቀን 09/04/2017ዓ/ም ከጥዋቱ 4:00 ሰኣት ላይ ተዘግቶ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን 09/04/2017ዓ/ም ጥዋት 4:30 ቢሮ ቁጥር 105 ይከፈታል።
➢ የጨረታማስከበርያ ዋስትና/ በተጫራቶች ምርጫ ከሚከተሉት ዓይነቶች አንዱ ሊሆን ይችላል። ሀ. በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና፣
ለ. በማይሻር ሌተር ኦፍ ክሬዲት የቀረበ ዋስትና፣
ሐ በአገር ውስጥ ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የክፍያ ትዕዛዝ፤ሁኖ 120,000.00(አንድ መቶ ሃያ ሺ ብር) ማስያዝ ኣለባቸው።
➢ የሚያሰፈልጉት የደኩመንት ብዛት ኦርጅናል ደኩመንት ከነ አንድ ኮፒ ለየብቻቸዉ በፖስታ በማሸግ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸዉ "
➢ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ያሉትን ቅፆች በትክክል በመሙላት፣ በያንዳንዱ የሰነዱ ቅፅ ፈርማ እና የድርጅቱ ማሕተም ማድረግ ኣለባቸው።
➢ ድርጅታችን ትግራይ መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ ይህ ጨረታ በማንኛውም ግዜ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኣድራሻ-ትግራይ መቐለ
ትግራይ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ
ቢሮ ቁጥር -----105 ግዥና ንብረት ኣስተዳደር
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር ----- 0342406380
ፋክስ ቁጥር 2510344402860/
Backs