ራያ ዩኒቨርስቲ ዳቦ፤ የተማሪዎች የምግብ ግብአት የሆኑ የፋብሪካ ውጤቶች፣ የተፈጨ በርበሬ፣ የተማሪዎች ሎከር እና ወንበር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
  • Posted Date: ቀዳሜ ጥቅምት 16, 2017 (about 1 month ago)
  • Closing Date: ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ቆይቶ በ16ኛው ቀን 4:00 ሰዓት
  • Bid Bond:ይለያያል በየ ሎቱ
  • location: ማይጨዉ
  • Bid Document Price:500.00
  • Bid Opening Date: ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ቆይቶ በ16ኛው ቀን 4:30 ሰዓት
  • Wood and Wood Work/ Food Items Supply/ Metals Works/ Aluminium Products and Works/
  • Print
  • Pdf

የብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር፡-ራዩ/ግአስአ/ግጨ-001/2017

ራያ ዩኒቨርስቲ ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተመለከቱትን ምድብ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ምድብየእቃው አገልግሎት ዓይነትየሰነድ መግዣ ዋጋየጨ/ማ ዋስትና መጠንየጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ዓይነትጨረታው አየር ላይ የሚቆይበትጨረታው የሚዘጋበት ቀንጨረታ የሚከፈትበት ቀን
ቀንሰዓት‍‍‍‍‌‍‌‍‌ ‌‍‍‍‌‍ቀንሰዓትቀንሰዓት
ምድብ 01ዳቦ50050,000.00ጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንከ የሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በህጋዊ ባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክረዲትከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን11:00በ16ኛው ቀን4:00በ16ኛው ቀን4:30
ምድብ 02የተማሪዎች የምግብ ግብአት የሆኑ የፋብሪካ ውጤቶች50030,000.00ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን11:00በ16ኛው ቀን4:00በ16ኛው ቀን4:30
ምድብ 03የተፈጨ በርበሬ50010,000.00ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን11:00በ16ኛው ቀን4:00በ16ኛው ቀን4:30
ምድብ 04የተማሪዎች ሎከር እና ወንበር50030,000.00ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን11:00በ16ኛው ቀን4:00በ16ኛው ቀን4:30

ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት እና ተጨማሪ ዝርዝር ጉዳዮችን በጨረታ ሰነዱ ላይ በመመልከት እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።

1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ የምዝገባ ሰርተፊኬት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል (ጊዜ ገደቡ ያላለፈበት) ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የሚሰጥ ታክስ ክሊራንስ፣ ጨረታ ማስከበርያ ዋስትና፣ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ EGP የተመዘገበ ወይም የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ማስረጃ፣ ሌሎች ዝርዝር የቴከኒክ መመዘኛዎች እንደየ ምድቡ ስለሚለያዩ በጨረታ ሰነዱ ላይ ይመልከቱ።

2. የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ምድብ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛውቀን 11፡00 ሰዓት ብቻ ራያ ዩኒቨርሲቲ ግዥ አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ ህንፃ ቁጥር 5፡ ምድር ቤት /ግራውንድ/ በመምጣት መግዛት ይችላሉ።

3. ከዋናው የጨረታ ሰነድ የሚያስፈልጉ የኮፒዎች ብዛት 1 ሲሆን በአጠቃላይ በ2 የተለያዩ ፖስታዎች ማለትም ዋና/ኦሪጅናል የሚል ምልክት ያለው የነዚሁ ሁሉም ሰነዶች ኮፒ ደግሞ በሌላ ፖስታ ቅጂ/ኮፒ የሚል ምልክት በማይለቅ ቀለም ተፅፎ ለየብቻው ታሽጎ የጨረታ ሳጥኑ ከመዘጋቱ በፊት በግዥ አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ ህንፃ ቁጥር 5 ግዥ ቡድን ምድር ቤት /ግራውንድ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።

4. ጨረታ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 በተራ ቁጥር 2 በተገለፀው አድራሻ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

5. ተጫራቾች አሸናፊ ለሆኑባቸው እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ዩኒቨርሲቲው ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።

6. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር 034 877 0501


Backs
Tender Category