ደደቢት ብድርና ቁጠባ ተቋም አ.ማ. የ2016 ዓ.ም. በጀት ዓመት የድርጅቱ የሥራ እንቅስቃሴ ወይም የሒሳብ ሥራ በውጭ ኦዲተሮች በጨረታ አወዳድሮ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል
  • Posted Date: ሰኞ መስከረም 27, 2017 (about 1 month ago)
  • Closing Date: ኣርብ ጥቅምት 1, 2017 04:00 Morning (closed)
  • Bid Bond:2%
  • location: መቐለ
  • Bid Document Price:200.00
  • Bid Opening Date: ኣርብ ጥቅምት 1, 2017 04:30 Morning
  • Accounting Related/ Auditing Related/
  • Print
  • Pdf

የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ማስታወቂያ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏

ደደቢት ብድርና ቁጠባ ተቋም አ/ማ የ2016 ዓ/ም በጀት ዓመት የድርጅቱ የሥራ እንቅስቃሴ ወይም የሒሳብ ሥራ በውጭ ኦዲተሮች በጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ አወዳድሮ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል። የሚከተለው መስፈርት የምታሟሉ የኦዲት ተቋማት /Audit firms/ እንድትወዳደሩ ድርጅታችን ይጋብዛል።

  1. ተጫራች በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መስፈርት መሰረት ከAABE (Accounting and Auditing Board of Ethiopia) ፍቃድ ያለው ሆኖ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርና ቫት ተመዝጋቢ መሆነ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  2. ተጫራች የ2016 ዓ/ም የሚገባውን የመንግስት ግብር የከፈለና የ2016 ዓ/ም ንግድ ፍቃድ ያሳደሰ መሆን አለበት።
  3. ተጫራች ለጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ው ማስከበርያ የሚሆን ከጠቅላላ ዋጋ ከ2% ያላነሰ በባንክ የተረጋገጠ በCPO ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል።
  4. ተጫራቹ ለኦዲት ሥራ በዝርዝር ከቀረቡለት ንኡስ ቅርጫፎች፣ ቅርጫፎችና ዋና መሥራቤቱ ጨምሮ በኣሰራሩ መሰረት ቢያንስ 50% /አምሳ በመቶ/ ኦዲት የሚደረጉ ሆነው በ2015 ዓ/ም በውጭ ኦዲተር ኦዲት ያልተደረጉ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ይሆናሉ።
  5. ከታች በተዘረዘሩት መስፈርቶች መሰረት ብቁ የሰው ሃይል በማዘጋጀት ለሥራ የሚሆኑ ሁለት ተሽከርካሪዎች ከድርጅታችን ተመድቦለት ሥራው ከተጀመረ በውኃላ በአንድ ወር ተኩል ወይም 45 ተከታታይ ቀናት ሥራውን ጨርሶ ለድርጅቱ ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት።
  6. ተወዳዳሪው በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መመርያ መሰረት ባለፉት ሁለት ተከታታይ ዓመታት በድርጅታችን የኦዲት ሥራ ያልተሳተፈ መሆን አለበት።
  7. የኦዲት ሥራ አስኪያጅ /Audit Manager/ በፋይናንስ ተቋማት በኦዲት ሥራ ሶስት/3/ ዓመትና ከዚያ በላይ የሥራ ልምድ ያለው ሆኖ ሁሉም የኦዲት አባላት ሰፊና ውስብስብ ሥራ ባላቸው የባንኮችና የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት የሒሳብ ሥራዎች ኦዲት በማድረግ በቂ እውቀትና ልምድ ያላቸው መሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  8. በኢ/ያ ብሄራዊ ባንክ ህግ መሰረት ሁሉም የኦዲት ቡድን አባላት የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርቲንግ ስታንዳርድ /IFRS/ መሰረት በማድረግ የሰለጠኑበት ሰርቲፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣ ከዚህ በተጨማሪ በ IFRS ሥራዎች በቂ እውቀትና ልምድ ያላቸው መሆን ይገባቸዋል።
  9. ተጫራች አሁን ባለው ሁኔታ በጥሩ አቋም የሚገኝ በህግ ያልታገደ ወይም ያልተከሰሰ፣ የመፍረስ አደጋ ያልተጋረጠበት መሆን አለበት።
  10. በኢ/ያ ብሄራዊ ባንክ መለክያዎች የኦዲት ቡድን አባላት በንብረት ዋጋ አወሳሰንና አተማመን በተመለከተ በቂ ስልጠና የወሰዱ እንዲሁም በእውቀት የተመሰረተ ትክክለኛና ፍትሃዊ ግምት ማስቀመጥ የሚችሉ ሰፊና ውስብስብ የማይክሮ ፋይናንስ ሥራዎችና የሚጠቀምባቸው አሰራሮች የመገምገምና የመረዳት ችሎታ ያላቸው መሆን ይገባቸዋል።
  11. በኢ/ያ ብሄራዊ ባንክ ኣሰራር መሰረት የኦዲት ቡድን አባላት የኦዲት ሥራው በትክክለኛ መንፈስና ነፃነት ሥራቸው ለማከናወን ሲባል ባለፉት ሶስት/3/ ዓመታት የማይክሮ ፋይናንሱ ሰራተኛ ያልነበሩ መሆናቸው ማረጋገጥ ይገባል።
  12. በኢ/ያ ብሄራዊ ባንክ የስነ ምግባር መስፈርት መሰረት በማድረግ የሚከተሉት አካላት የውጭ ኦዲት አጋር ወይም አባላት አለመሆናቸው በሚቀርብለት ቃለ-ማሃላ ማረጋገጥ የሚችል።
  1. ኦዲት ለሚደረገው ተቋም ባለ አክስዮን /Shareholder/፣ ዳይሬክተር ወይም የማይክሮ ፋይናንስ ሰራተኛ አለመሆናቸው፣
  2. በፍርድ ቤት ያልተገባ ሥራ በመሥራት ኪሰራ የታወጀበት አለመሆነ
  3. በማንኛውም ወንጀል ወይም የወንጀል ድርጊት ማለት በማጭበርበር ወይም በማታለል፣ በገንዘብ ወንጀል ወይም በሌሎች ህገወጥ ተግባራት በመሳተፍ በፍርድ ቤት ያልተፈረደባቸው መሆናቸው፣
  4. በማንኛውም የማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ወይም በሌላ የገንዘብ ተቋም አባል አለመሆናቸው
  5. በማንኛውም የግብር ግዴታ ተጠያቂ አለመሆናቸው ማረጋገጥ የሚችል።

13. በኢ/ያ ብሄራዊ ባንክ የውጭ ኦዲተሮች መርህ መሰረት የውጭ ኦዲተር፣ የሥራ አጋሮቹ ወይም የሒሳብ ቡድን አባላት እንዲሁም ተባባሪዎቻቸው ምንም ዓይነት የተቀማጭ ሒሳብ እንዳይሰሩና በክንድ ርዝመት ካልሆነ በስተቀር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተበዳሪ ወይም የማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ተጠቃሚ አለመሆናቸው ማረጋገጥ ይገበዋል።

14. በኢ/ያ ብሄራዊ ባንክ መስፈርቶች መሰረት በኦዲት ውል ላይ አንድ የኦዲት ድርጅቱ በባለቤትነት፣ በዳይሬክቶሮችና በሥራ አስኪያጆች ላይ በሚኖረው ለውጥ ምክንያት በዚህ መመርያ ላይ የተቀመጠውን መስፈርት ሳይፈፅም ከቀረ እንዲሁም በድርጅቱ ወይም በማናቸውም የሒሳብ ቡድኑ አባላት ላይ የሚወሰድ ማናቸውም ዲስፕሊን ወይም ህጋዊ እርምጃ ውሉ ሊሰረዝ እንደሚችል በግልፅ መታወቅ አለበት።

15. በኢ/ያ ብሄራዊ ባንክ መመርያ በሚያዝዘው መሰረት አንድ የውጭ ኦዲተር ለእያንዳንዱ ቀጠሮ ወይም ዳግም ቀጠሮ በዚህ መመርያ Annex I እና II መሰረት ቀደም ተከተል የፃፈውን የነፃነት ማረጋገጫ እና ተገቢ አዋጅና ፎርም አክብረው ጨርሰው እንዲያቀርቡ ያስፈልጋል።

16. ተጫራቾች የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ው ሰነድ ከመስከረም22/01/2017 ዓም ጀምሮ ከደደቢት ብድርና ቁጠባ ተቋም ዋና መስሪያቤት መቐለ ቅርጫፍ ቁጥር 2 ከሚገኘው ፅ/ቤታችንና አዲስ አበባ ከሚገኘው ላይዘን ፅ/ቤታችን 22 ፊትለፊት ፅጌ ሽሮ ቤት 200 ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

17. የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ሰጥን ክፍት ሆኖ የሚቆየው ከመስከረም 22/01/2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 01/02/2017 ዓ/ም ከጥዋቱ 4፡00 ሆኖ የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ሳጥን በዚህ ቀን 4፡00 ሰዓት‍‍‍‍‌‍‌‍‌‌‌‍‍‍‌‍ ተዘግቶ በ4፡30 ተጨራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደደቢት ብድርና ቁጠባ ተቋም ኣ/ማ በ4ኛው ፎቅ የፋይናንስ ክፍልና በአዲስ በአዲስ አበባ ለይዘን ኦፊ ይከፈታል:: ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ህጋዊነቱ እስከ ጠበቀ ድረስ ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ው የሚከፈት ይሆናል።

18. የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ው አሸናፊ የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ው ውጤት ከተገለፀ በውኃላ በ 7 ተከተታይ ቀናት ውስጥ ወደ ድርጅቱ የንብረትና ግዢ አስተዳደር ቀርቦ ውል ማሰር አለበት።

19. የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ው አሸናፊ የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ው ውጤት ከታወቀ በውኃላ ከጠቅላላ ዋጋ 10% unconditional bank guarantee ማስያዝ አለበት።

20. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ው ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በሞባይል ቁጥር መቐለ ዋና ቢሮ +251 963 095 665 አዲስ አበባ ላይዘን ኦፊስ +251 928 277 756 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።


Backs
Tender Category