የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር AK/NU/PPAD/3806/02/2016
አክሱም ዩኒቨርሲቲ ቀጥሎ የተገለፁቱን የእቃዎች አቅርቦት ግዥ ከህጋዊ ነጋዴዎች በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የእቃዎች አቅርቦት ገዥ ዝርዝር፤
ተ.ቁ | የጨረታ ሰነድ ቁጥር /ሎት/ | የጨረታ ዓይነት | የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ በብር | የጨረታ ማስከበሪያ መጠን በብር |
1 | 24 | የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች | 500.00 | 40,000.00 |
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ለእቃዎች ግዥ በዩኒቨርሲቲው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከግዥ ክፍል፣ ህንፃ ቁጥር 53፣ ቢሮ ቁጥር 002፣ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
1. ተጫራቾች በሥራው መስከ የተሰማሩና ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው መሆኑን የሚያስረዳና በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ማስረጃዎችን ማያያዝ አለባቸው።
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የግብር ከፋይ
መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
3. ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆኑን ማስረጃ ማያያዝ አለባቸው፡፡
4. ለጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት 3% ልዩ አስተያየት ይደረጋል፡፡
5. ጨረታው የሚከፈተው የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ካሉት 15 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው ቀጣይ የሥራ ቀን ሆኖ በጨረታ ሰነዱ በተገለፀው ቀንና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በግልጽ በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ይከፈታል፡፡
6. የተጫራቾች ወይም የህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታው መከፈት አይስተጓጎልም፡፡
7. የጨረታው አሸናፊ በጊዜው ቀርቦ ውል የማያስር ከሆነ በጨረታ ሰነዱ የተገለጸው። ለጨረታ ማስከበሪያነት ያስያዘውን ገንዘብ አይመለሰለትም፡፡
8. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ
በስልክ ቁጥር፡- 0913 57 45 60/0914 77 43 40 ደውለው ይጠይቁ
አክሱም ዩኒቨርሲቲ
Backs