የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐለ ዲስትሪከት የሰሊጥ እርሻ ድርጅት ላይ ያለውን የመጠቀም መብት እና አንድ የእርሻ ትራክተር በሐራጅ ለመሸጥ ይፈልጋል
  • Posted Date: እሁድ ሚያዝያ 11, 2012 (over 4 years ago)
  • Closing Date: ማክሰኞ ግንቦት 11, 2012 06:00 Morning (closed)
  • Bid Bond:0.00
  • location: መቐለ
  • Bid Document Price:0.00
  • Bid Opening Date: ማክሰኞ ግንቦት 11, 2012 06:01 Morning
  • House & Building Sale/ Other Sale/
  • Print
  • Pdf

ስማቸው ከዚህ በታች የተገለጸው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐለ ዲስትሪከት ተበዳሪ ከባንኩ የወሰዱትን የብድር ገንዘብ ወቅቱን ጠብቀው ተመላሽ ባለማድረጋቸው ምክንያት ባንኩ በአዋጅ ቁጥር 97/98፣ 98/90 እና 216/92 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለብድሩ አመላለስ መያዣ የሆነው ቀጥሎ የተመለከተው ፕሮጀክት ከጠቅላላ ንብረቱ ጋር በሐራጅ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የሐራጁ ዝርዝር መረጃ

የተበዳሪው/የመያዣ ሰጪው ስም

የሚሸጠው ንብረት አድራሻና አይነት

የሐራጁ ደረጃ

የሐራጁ መነሻ ዋጋ /ብር/

ጨረታው የሚከናወንበት ቀንና ሰዓት

ወ/ሮ አኸበረት ገ/ፃዲቕ ገ/ጊዮርጊስ

በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምዕራባዊ ዞን ፣ ቀፍታ ሑመራ ወረዳ፣ማይካድራ ቀበሌ ፣ ልዩ ስሙ ባሕረሰላም ውስጥ 600 ሄክታር ቦታ ላይ የተቋቋመ የሰሊጥ እርሻ ድርጅት ላይ ያለውን የመጠቀም መብት እና አንድ የእርሻ ትራክተር

የመጀመሪያ

4,550,91415 / ለእርሻ መሬቱ ማልማት የወጣ ወጪ ግምት 750,199.92 / የትራክተር ወቅታዊ ግምት /በድምሩ የሐራጁ መነሻ ዋጋ 5,301,114.07

ግንቦት 11 ቀን 2012 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00-6፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ

ማሳሰቢያ:-

  1. 1. ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ(CPO) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
  2. 2. ሐራጁ የሚካሄደው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሑመራ ቅርንጫፍ ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው:: .
  3. 3. የሐራጁ አሸናፊ ያሽነፈበትን ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሰው ቀን ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
  4. 4. አሸናፊው ያስያዘው ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸነፉ ተጫራቶች ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል።
  5. 5. 15% የተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ ታክስና ግብሮችን ፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው /የጨረታ አሸናፊው/ይከፍላል፡፡
  6. 6. ሐራጁ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው፣ ተበዳሪዎች፥ አስያዥች እና የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ተወካዮች በተገኙበት በግልፅ ይከናወናል፣
  7. 7. ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐለ ዲስትሪክት በሚገኘው የፕሮጀክት ማስታመሚያና ብድር ማገገሚያ ቡድን በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር ፡- 0344-419016 ወይም 0344-407439 ደውሎ ማግኘት ይቻላል፡፡ ፕሮጀክቱን በሥራ ሰዓት መ'ኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከቡድኑ ጋር በመነጋገር መጐብኘት ይቻላል፡፡
  8. 8. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ሐራጁን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐለ ዲስትሪክት

Backs
Tender Category