ጨረታዉ በኣዲስ ዘመን ጋዜጣ የወጣበት ቀን 24/6/2012
ጨረታዉ የሚዘጋበት ቀን : በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት
ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን: በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት
የጨረታ መስያ ቁጥር ራዩ/ግስዳ/005/2012
ምድብ | የእቃው/ አገልግሎቱ አይነት | የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠን | የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አይነት | ጨረታው የሚዘጋበት ቀን | ጨረታው የሚከፈትበት ቀን |
ቀን | ሰዓት | ቀን | ሰዓት |
ምድብ 1 | የቪዲዮ ካሜራ እና መለዋወጫ ዕቃ ግዢ | 50,000.00 | ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከዋጋ ሰነድ ጋር የሚቀርብ | በ16ኛው ቀን | 4፡00 | በ16ኛው ቀን | 4፡30 |
ምድብ 2 | የጣት አሻራ ማሽን ግዢ (Finger Print Machine) | 75,000.00 | በ16ኛው ቀን | 4፡00 | በ16ኛው ቀን | 4፡30 |
ምድብ 3 | የሩዝ አቅርቦት ግዢ | 10,000.00 | በ16ኛው ቀን | 4፡00 | በ16ኛው ቀን | 4፡30 |
ምድብ 4 | ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ትራክተር መኪና ግዢ | 120,000.00 | በ16ኛው ቀን | 4፡00 | በ16ኛው ቀን | 4፡30 |
ምድብ 4 | ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የጽዳትና ንጽህና መጠበቂያ ግዢ | 50,000.00 | በ16ኛው ቀን | 4፡00 | በ16ኛው ቀን | 4፡30 |
ራያ ዩኒቨርሲቲ ከላይ በሰንጠረዡ የተመለከተውን ምድብ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባችሁ፡፡
- 1. ተጫራቾች የ2012 ዓ.ም ህጋዊ ለምድቡ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን ጊዜ ገደቡ ያላለፈበት የተሰጠ የምስክር ወረቀት ወይም ታከስ ከሊራንስ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና በፌዴራል የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ በዌብሳይታቸው በእቃ/በአገልግሎት አቅራቢነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- 2. ተጫራቾች ለየምድቡ የጨረታ ሰነድ መሸጫ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ አድሚን ህንፃ ቁጥር 5 ግዥ ቡድን 2ኛ ፎቅ ዘወትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- 3. ተጫራቾች ለሁሉም ምድብ ቴክኒካል አንድ ዋና እና አንድ ኮፒ እንዲሁም አንድ ፋይናንሻል ዋና እና ኮፒ በተለያየ 4 ፖስታ በማሸግ እንዲሁም የጨረታው ዓይነት በደማቅ ጽሁም በመጻፍ የጨረታ ሳጥኑ ከመዘጋቱ በፊት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ከላይ በተራ ቁጥር 2 በተመለከተው አድራሻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- 4. ጨረታው በ16ኛ ቀን ልክ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ ውስጥ በግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አድሚን ህንፃ ቁጥር 5 ግዥ ቡድን 2ኛ ፎቅ ይከፈታል ነገር ግን 16ኛ ቀን ሃይማኖታዊ ወይም መንግስታዊ በዓል ከሆነ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- 5. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ይህ ጨረታ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ20 ቀናት ይሆናል፡፡
- 6. የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ ባንከ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት በቴክኒካል ፖስታ ውስጥ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- 7. አሸናፊ ተጫራች ዕቃዎችን በራሱ ትራንስፖርት እስከ ራያ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
- 8. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- 9. ለበለጠ መረጃ www.rayu.or ወይም በስልክ 03 42 47 29 27/03 42 47 83 75 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
Backs