በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ዕዝ የ8ኛ ሜ/ክ/ጦር ጠ/ መምሪያ ለቋሚና ለኮንትራት ሠራተኞች አልባሳት፣አላቂ የፅህፈት መሳሪያ፣ልዩ ልዩ የፅዳት ማቴሪያል፣ጀዲድ፤ ሻሽ እና ቁጢት፣የቀላል ተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ለኦፊስ ማሽን ጥገና መለዋወጫ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
  • ለቋሚና ለኮንትራት ሠራተኞች አልባሳት
  • አላቂ የፅህፈት መሳሪያ
  • ልዩልዩ የፅዳት ማቴሪያል
  • ጀዲድ፤ ሻሽ እና ቁጢት
  • የቀላል ተሽከርካሪ መለዋወጫ
  • ለኦፊስ ማሽን ጥገና መለዋወጫ

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ሕጋዊ ነጋዴ ተጫራቾች በጨረታው ሊወዳደሩ

ይችላሉ ፡፡

  1. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው የጨረታ ዓይነቶች ህጋዊ የታደሰ ን/ፍቃድ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት፣ የቫት ሰርተፊኬት የአቅራቢነት ሰርተፊኬት እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸውን ያወዳድራል፡፡
  2. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ለእያንዳንዳቸው ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መመሪያ መሰረት በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የዕቃውን ዓይነት በዋጋ ማቅረቢያው ላይ በግልፅ ያለምንም ስርዝ ድልዝ መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. የጨረታ ሰነዱን ከተጫራቾች ዝርዝር መመሪያ ጋር የማይመለስ 100.00 ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት የሥራ ቀናት ውስጥ ዓዲ-ሃገራይ የ8 ሜ/ክ/ ጦር ጠ/መምሪያ ግዥ ዴስክ ቢሮ መግዛት ይቻላል፡፡
  • አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲፈፅሙ የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል ::
  • ያሸነፉትን ዕቃ በራሳቸው ውጪ በማጓጓዝና ለማራገፍ ዓዲሃገራይ የ8ኛ ሜ/ክ/ጦር ጠ/መምሪያ ግምጃ ቤት ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ እንዲሁም 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው::
  • ጨረታው የካቲት 13/2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የክ/ጦሩ ግዥ ዴስክ በሚያዘጋጀው ቦታ ይከፈታል፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0911025079 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ።

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ዕዝ

ጠቅላይ  መምሪያ የ8ኛ ሜ/ክ/ጦር መ/መምሪያ

Backs
Tender Category