በትግራይ ክልል ኮንስትራክሽን መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ዳይሬክቶሬት መንገድ ልማትና አስተዳደር የመንገድ ጥገና ሥራ የኮንሰልታንሲ ሰርቪስ ግልፅ ጨረታ ማሰራት ይፈልጋል
  • Posted Date: ሓሙስ ታኅሣሥ 30, 2012 (over 5 years ago)
  • Closing Date: እሁድ ጥር 17, 2012 04:00 Morning (closed)
  • Bid Bond:20000.00
  • location: መቐለ
  • Bid Document Price:200.00
  • Bid Opening Date: ሮብ የካቲት 18, 2012 06:00 Afternoon
  • Engineering Related Consultancy/
  • Print
  • Pdf
  1. የኢትዮጵያ መንገድ ፈንድ በትግራይ ክልል ለሚገኙ የገጠርና ከተማ የመንገድ ኤጀንሲዎች ለመንገድ ጥገና የ2012 ዓመት በጀት የመደበ ሲሆን ከዚሁ ከተመደበው በጀት ውስጥ ለመንገድ ኤጀንሲዎች የሚሠት የመንገድ ጥገና ሥራ የኮንሰልታንሲ ሰርቪስ ግልፅ ጨረታ አጫርቶ ለኢትዮጵያ መንገድ ፈንድ እንዲያቀርቡ የትግራይ ክልል ኮንስትራክሽን መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መንገድ ልማትና አስተዳደር ከኢትዮጵያ መንገድ ፈንድ ፅ/ቤት በተሰጠው ሙሉ ውክልና መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት ማሟላት የሚችሉ ሁሉ በግልፅ ጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
  2. የ2011 ዓ.ም የአማካሪነት ንግድ ሥራፍቃድ ተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለፈው ወር ዲክላሬሽን የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር /Tin No /የታደሰ የአቅራቢዎች ምስክር ወረቀት ፈቃድ ያላቸው ሕጋዊ አማካሪዎች በተጨማሪ ከኮንስትራክሽን ሚኒስተር ወይም ውክልና ከተሰጠው አካል የ2012 ዓ.ም የታደሰ የአማካሪነት ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፡፡
  3. በመንገድ ፈንድ ሙሉ ውክልና የተሰጠው የትግራይ ክልል ኮንስትራክሽን መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ዳይሬክቶሬት የመንገድ ልማትና አስተዳደር በ (Highway and bridge consultancy and construction management consultancy) ደረጃ -3 እና ከዚህ በላይ አማካሪዎች፡፡
  4. ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፈቀደላቸው ከታወቁ ባንክ በሚሰጥ የተረጋገጠ ያለገደብ (Unconditional bank guarantee) ሲፒኦ ወይ በካሽ ብር 20,000.00 ብር /ሃያ ሺህ ብር / ቢሮ ኮንስትራክሽን መንገድ ትራንስፖርት ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች ለተጫረቱበት Consultancy Service for the Supervision and Contract Administration of Road Maintenance Program for Tigray region Urban and Agencies የሥራ ውል ከተፈጸረመበት ቀን ጀምሮ በትንሹ ለአሥራ ሁለት ተከታታይ ወራት /365 ቀናት/ ሙሉ በሙሉ ሥራውን መስራት አለበት፡፡
  6.  ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከ17/04/2012 ዓ.ም ጀምሮ ከትግራይ ክልል ኮንስትራክሽን መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ዳይሬክቶሬት የመንገድ ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 152 አስፈላጊውን ማስረጃ በማስያዝ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የሚጫረቱበት የኮንሰልታንሲ ሰርቪስ ዋጋ ፋይናንሻል/ እና ቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል ሁለት ፎቶ ኮፒ እያንዳንዳቸው በተለያዩ ፖስታዎች ታሽገው የ2011 ዓ.ም የታደሰ የአማካሪነት ንግድ ስራ ፍቃድ የባለፈው ወር ዲክላሬሽን የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Time No / የአቅራቢዎች ምስክር ወረቀት ፈቃድ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለያንዳንዳቸው በፖስታ በማሸግ እንዲሁም ሁሉንም ጠቅልሎ በሚይዝ ትልቅ ፖስታ ላይ በሚታይ ፅሁፍ ተፅፎ በትግራይ ክልል ኮንስትራክሽን መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ በዳይሬክቶሬትመንገድልማትና አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 152 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ተከታታይ ቀን /31ኛውን ጨምሮ/እስከ 17/05/2012 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  8. ጨረታው የሚዘጋበት ቀን በ17/05/2012 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ከሰዓት በፊት ሆኖ በተመሳሳይ ቀን 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 152 በጨረታ ኮሚቴ ፊት ይከፈታል።
  9. ተጫራቾች ወደ ዋጋ/financial/ መወዳደሪያ ሰነድ ለመግባት ዝቅተኛው የቴክኒካል ነጥብ 70% /ሰባ ፐርሰንት /ማግኘት አለባቸው የቴክኒካል ዝቅተኛ ነጥብ ያላገኙ ተጫራቾች የዋጋ መወዳደሪያ ሰነዳቸው ሳይከፈት ይመለሰላቸዋል፡፡
  10. ቢሮው የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሠረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ለበለጠ መረጃ ለዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መንገድ ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 210 ሦስተኛ ፎቅ ወይም

አድራሻ ስልክ ቁጥር፡- 0344-41-06-45/0344-40-00-50

ፖሳ.ቁ 225

 መቐለ

 ትግራይ

 ኢትዮጵያ

በትግራይ ክልል ኮንስትራክሽን

 መንገድ ትራንስፖርት 

ቢሮ ዳይሬክቶሬት መንገድ 

ልማትና አስተዳደር

Backs
Tender Category