ድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር: ERCCMB/NCB004/2012
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን መቐለ ቅ/ጽ/ቤት ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የሚከተለውን አገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
- ሎት አንድ፣ የመኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ቲን ሰርተፊኬት ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ ር አቅራቢነት ፍቃድ ወይም በክልል እቅድና ፋይናንስ ቢሮ የተሰጠ የአቅራቢነት ፈቃድ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
- ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ማስከበርያ ብር 10,000.00/አስር ሺህ /በባንክ በተመሠከረለት ቼክ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም ጥሬ ገንዘብ ከጨረታው መክፈቻ በፊት ማቅረብ ይኖርባችኋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ ኢ/ያ አጠገብ የሚገኘው የውሃንስ ግደይ ህንፃ ላይ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1 ማስገባት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ታህሳስ 11 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታውም በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4:30 በመስሪያ ቤቱ ሁለተኛ ፎቅ ሃብት አስተዳደር ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- የጨረታው አሸናፊ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና 10% (አስር በመቶ) CPO ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 03424071162/0919068385/0914830469
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የመቐለ ቅ/ፅ/ቤት
መመለስ