ፋብሪካችን ሞሓ የለስላሳ መጠጦች ኢንዳስትሪ አክስዩን ማህበር መቐለ ፔፕሲ ኮላ ፋብሪካ ለፋብሪካው ኣገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ብረታ ብረቶች / የህንፃ መሳሪያዎች/ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
  • የተለቀቀበት ቀን: ኣርብ ሐምሌ 12, 2011 (ከ 5 ዓመታት)
  • መዝግያ ቀን: ኣርብ ሐምሌ 19, 2011 08:15 ከሰአት (ተዘጋ)
  • የጨረታ ማስከበርያ ዋጋ:2%
  • ቦታ: መቐለ
  • የጨረታ ደኩመንት ዋጋ:50.00
  • ጨረታ ሚከፈትበት ቀንና ሰዓት: ኣርብ ሐምሌ 19, 2011 08:30 ከሰአት
  • ህንፃ መሳርሒ/ ሰራሕቲ ሓፂነ መፂን/
  • Print
  • Pdf

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መምርያ ኣክብራችሁ መወዳደር የምትችሉ ተጫራቾች ሁሉ መጫረት የምትችሉ መሆኑ በኣክብሮት እንገልፃለን።

የጨረታ መምርያ

1 ተጫራቾች በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ : የኣቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት: የቫት ተመዝጋቢ መሆኑ የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት እና ቲን ምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2 ተጫራቾች ለጨረታዉ ማስከበሪያ የጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 2 በመቶ የገንዘብ ክፍያ ማዘዣ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል ።

3 ተጫራቾች የሚቀርቡትን ዋጋ ቫት ያካተተ ሙሆኑን እና አለመሆኑን በግልፅ መቀመጥ ይኖርባቸዋል። ይህ ካልሆነ ግን ዋጋዉ ቫትን ያካተተ መሆኑ ታሳቢ ይደረጋል።

4 የጨረታዉ ዝርዝር ሰነድ ከድርጅቱ ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 12 ድረስ በመምጣት እና ብር 50.00 በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይቻላል።

5 ተጫረቾች ዋጋቸዉ በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህን ጨረታ ከወጣበት ግዜ ጀምሮ እስከ 19/11/2011 ዓ/ም በስራ ቀንና ሰዓት ኣክሱም ሆቴል ፊት ለፊት ከሚገኘዉ ዋና ቢሮኣችን ድረስ በመምጣት ለዚሁ ተብሎ በተዘገጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ እና የሰነዱ ማሽግያ ፖስታ ተጫራቾች ህጋዊ ማህተምና እና ፊርማ መኖር ይኖርበታል።

6 የጨረታ ሳጥኑ 19/11/2011 ዓ/ም ከቀኑ 8:15 የሚታሸግ ሲሆን ከዚሁ ሰዓት ባኃላ የጨረታ ሰነድ የሚመጣ ተቀባይነት ኣይኖረዉም።

7 ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት/ ባልተገኙበትም 19/11/2011 ዓ/ም ከቀኑ ልክ 8:30 በፋብሪካዉ የግዥና ክምችት መምሪያ ቢሮ ወስጥ ይከፈታል።

8 ተጫራቾች ማሸነፋቸዉ እንደተነገራቸዉ በ7 ቀናት ወስጥ እቃዎችን የማስረከብ ግዴታ ይኖርባቸዋል።ይህ ሳይሆን ሲቀር ግን ያስያዘዉ የዉል የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ካለ ምንም ቅድመ ሆኔታ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።

9 ማንኛዉም ተጫራች ጨረታዉ ከተከፈተ ባኃላ ጨረታዉን መሰረዝ ኣይችልም።

10 ስርዝ ድልዝ የሆነ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረዉም።

11 ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በማንኛዉም ግዜ ጨረታዉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

ለበለጠ መረጃ 0342-415205/ 0344-415214/ 0342-415070 መደወል ይቻላል፡፡

መመለስ
የጨረታ ምድብ