ሞሓ የለስላሳ መጠጦች ኢንዳስትሪ አክስዩን ማህበር መቐለ ፔፕሲ ኮላ ፋብሪካ በቃላሚኖ ኣካባቢ የውሃ መስመር ዝርጋታ ስራ በውሃ ነክ ስራዎች ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ ኣወዳደሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
  • የተለቀቀበት ቀን: ሰኞ ታኅሣሥ 8, 2011 (ከ 6 ዓመታት)
  • መዝግያ ቀን: ሮብ ታኅሣሥ 17, 2011 08:15 ከሰአት (ተዘጋ)
  • የጨረታ ማስከበርያ ዋጋ:2%
  • ቦታ: መቐለ
  • የጨረታ ደኩመንት ዋጋ:50.00
  • ጨረታ ሚከፈትበት ቀንና ሰዓት: ሮብ ታኅሣሥ 17, 2011 08:30 ከሰአት
  • ስራሕቲ ማይ/
  • Print
  • Pdf

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መምርያ ኣክብራችሁ መወዳደር የምትችሉ ተጫራቾች ሁሉ መጫረት የምትችሉ መሆኑ በኣክብሮት እንገልፃለን።

የጨረታ መምርያ                                    

1 የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው እና የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤

2 ተጫራቾች ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ኣለባቸው።

3 ደረጃቸው ከደረጃ ስድስት በላይ የሆኑ እና ከኣሁን በፊት በውሃ ነክ ስራዎች የሰርዋቸው ቢያንስ ሁለት ዓይነት ስራዎች የስራ ልምድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤

4 እላይ ቁጥር 1-3 የተገለፁት ሰነዶች ኦርጅናል ዶክመንት እና ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፤

5 ተጫራቾች ለጨረታዉ ማስከበሪያ የጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 2% የገንዘብ ክፍያ ማዘዣ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል ።

6 ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኣክሱም ፊት ለፊት ከሚገኘው ሞሓ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ኣ/ማ መቐለ ፔፕሲ ኮላ ፋብሪካ ቢሮ ቁጥር 15 ድረስ በመምጣት  እና የማይመለስ ብር 50.00 በመክፈል የጨረታ ሰነዱ በመውሰድና የሚሰሩበትን ነጠላ ዋጋ ከነቫቱ በተቀመጠው ፎርማት መሰረት በማስቀመጥ እና በታሸገ ኢንቨሎፕ በመክተት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ከ 05/04/2011 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 17/04/2011 ዓ/ም በዚሁ ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ማሰገባት ይችላሉ።

7 የጨረታ ሳጥኑ ታሕሳስ 17/2011 ዓ/ም ከቀኑ 8:15 የሚታሸግ ሲሆን ከዚሁ ሰዓት ባኃላ የጨረታ ሰነድ የሚመጣ ተቀባይነት ኣይኖረዉም።

8 ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት/ ባልተገኙበትም 17/04/2011 ዓ/ም ከቀኑ ልክ 8:30 በፋብሪካዉ የግዥና ክምችት መምሪያ ቢሮ ወስጥ ይከፈታል።

9 ተጫራቾች ማሸነፋቸዉ እንደተነገራቸዉ በ 3 ቀናት ወስጥ የጠቅላላ ክፍያ 10% ሲፒኦ በማሰራት ለውል ማስከበሪያ በማቅረብ ውል የማሰር ግዴታ ኣለባቸው።

10 ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በማንኛዉም ግዜ ጨረታዉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

መመለስ
የጨረታ ምድብ