ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 02/2011
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ህፀተ ዝናብ ግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ ለ2011 ዓ.ም ለመማርና ማስተማር አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የላብራቶሪ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፡-
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለውና ፍቃዱንም በ2011 ዓ.ም የታደሰ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- በቀረበው ዝርዝር ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ የሚችል።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል።
- ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ለተወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ የጠቅላላው ዋጋ 24,000.00 (ሃያ አራት ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ስም ማስያዝ የሚችል።
- ማንኛውም ተጫራች የማይመለስ ብር 50.00 (ሃምሣ ብር) በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ በህፀተ ዝናብ ግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ ግዥ ፋይናንስና ፋስልቲ ማናጅመንት ቡድን ቢሮ ቁጥር H-4 መውሰድ ይችላል።
- አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈው ዕቃ በራሱ ወጪና ትራንስፖርት ዕቃዎቹ ዋና ግቢ ኮሌጅ ማድረስ አለበት።
- ተጫራቾች ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በህፀተ ዝናብ ግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ ግዥ ፋይናንስና ፋስልቲ ማናጅመንት ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የግልፅ ጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው ከወጣበት በ20ኛው ቀን ጠዋት 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በቀኑ ልክ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ ይከፈታል። በ20ኛው ቀን በዓል ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ ይከፈታል።
- በጨረታው አሸንፎ በወቅቱ ውል ለማያስር የጨረታ አሸናፊ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ውርስ ይሆናል።
- ኮሌጅ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0914 72 16 27 ወይም 034 241 17 78 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል።
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ህፀተ ዝናብ ግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ
መመለስ