የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ለትምህርት ስርጭት ቀረፃ የሚያገለግል BACK UP ፕላዝማ ኔትዎርክ ዝርጋታ ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት /ለመዘርጋት/ ይፈልጋል
  1. ለትምህርት ስርጭት ቀረፃ የሚያገለግል BACK UP
  2. ፕላዝማ ኔትዎርክ ዝርጋታ ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት /ለመዘርጋት/ ይፈልጋል

ስለዚህ በዚህ ግልፅ ጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ፡-

  1. ጨረታው በተመለከተ ንግድ ፍቃድ ያለውና የ2010 ዓ.ም ያሳደሰ መሆን አለበት፡፡
  2. በአቅራቢነት የተመዘገበ ቲን ቁጥር ያለው እንዲሁም ነሃሴ ወር /2010 ዓ.ም ቫት ዲክላሬሽን የሚያቀርብ መሆን አለበት።
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ለBACK UP 5,000 ( አምስት ሺ ብር ) ማስያዝ ለፕላዝማ ኔትዎርክ ዝርጋታ ስራ ደግሞ 72,000.00 ( ሰባ ሁለት ሺ) በCPO ማቅረብ አለባቸው።
  4. ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት መቐለ ከሚገኘው ከትግራይ ክልል ትም/ቢሮ ህንፃ 1ኛው ፎቅ ግዥ ክፍል የማይመለስ ለእያንዳንዱ ጨረታ ዶክሜንት ብር 100.00 በመክፈል መውሰድ ይቻላል፡፡
  5. ለBACK UP የጨረታ አሸናፊ ውል ከፈፀመበት ጊዜ ጀምሮ በተከታታይ 60 ቀናት ውስጥ በተሰጠው ስፔስፊኬሽን መሰረት በትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ገቢ ማድረግ አለበት እንዲሁም ፕላዝማ ኔት ዎርክ ዝርጋታ ስራ በተሰጠው ስፔስፍኬሽን መሰረት በ90ና ተከታታይ ቀናት ውስጥ ሰርቶ ማስረከብ ይጠበቅበታል።
  6. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በተከታታይ እስከ 15ኛው ቀን 8፡30 ሰዓት ድረስ በትግራይ ክልል ትም/ቢሮ 1ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን የጨረታ ዶክመንት ማስገባት ይገባል።
  7. ጨረታው በ15ኛው ቀን በ8፡45 ዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል በተገኙበት ይከፈታል። 15ኛው ቀን በዓል ከዋለ ግን በሚቀጥለው የስራ ቀን የመዝጊያና የመክፈቻ ቀን ይሆናል።
  8. ተጫራቾች ጨረታ ዶክመንት ቴክኒካልና ፋይናንሻል ኦርጅናል ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው።
  9. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር

    0344-40-34-77/0344408299 በመደወል መጠየቅ ወይም በትግራይ ክልል ትም/ት ቢሮ ዌብ ሳይት WWW.tigray.educ.com ማየት ይቻላል።
መመለስ
የጨረታ ምድብ