የኢትዩያ ኦርተዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የልማት ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የኽልተ አዉላዕሎ የገኑማፕሮጀክት ለመስኖ ግልጋሎት የሚዉል የኤሌክትሪክ ዲናሞ ፓምፕ ለመግዛት ስለተፈለገ
  • የተለቀቀበት ቀን: ሓሙስ ጥር 21, 2007 (ከ 10 ዓመታት)
  • መዝግያ ቀን: ሮብ ጥር 27, 2007 06:00 ከሰአት (ተዘጋ)
  • የጨረታ ማስከበርያ ዋጋ:0.00
  • ቦታ: መቐለ
  • የጨረታ ደኩመንት ዋጋ:0.00
  • ጨረታ ሚከፈትበት ቀንና ሰዓት: ማክሰኞ 5, 2005 06:00 ከሰአት
  • ጠቅላላ ስራሕቲ ኣገልግሎት/
  • Print
  • Pdf

ብድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዩያ ኦርተዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የልማት ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የኽልተ አዉላዕሎ የገኑማፕሮጀክት ለመስኖ ግልጋሎት የሚዉል የኤሌክትሪክ ዲናሞ ፓምፕ ለመግዛት ስለተፈለገ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሞሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል::

  1. አቅራቢነት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸዉ::

  2. የ2006 ዓ/ም ግብር የከፈሉና የዓመት ፍቃድ ያሳደሱ::

  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ የሆኑና ያለፈዉ ወር ተእታ የከፈሉበት መረጃ ማቅረብ የሚችሉ::

  4. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1- 3 የተጠቀሱት መረጃዎች ኦርጅናልን በመያዝ የጨረታ ሰነድ መግዛት አለባቸዉ

  5. ተጫራቾች የጨረታዉን ሰነድ በማይመለስ 20.00 / ሃያ ብር/ በመግዛት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 / አስር / ቀናት ዉስጥ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ::

  6. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000 /አምስት ሺ ብር / የባንክ ዋስትና ወይም CPO ማቅረብ የሚችሉ::

  7. ዕቃዉ ዉል ከተፈፀመ ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ሙሉ ለሙሉ ማስረከብ የሚችሉ::

  8. ተሞልቶ የሚቀርበዉ ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለበትና በድርጅታችን በተዘጋጀዉ የጨረታ ሰነድ ብቻ ተሞልቶ መቅረብ አለበት ይህንን ያላሞላ ከጨረታዉ ይስረዛል::

  9. የጨረታዉ የቴክኒክና ዋናዉና ቅጂ ሰነድ ለየብቻዉ የፋይናንስ ሰነድ ዋናዉና ቅጂ ለየብቻዉ በስም በታሸገ ኢንቨሎፕ ለጨረታዉ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ያስፈልጋል::

  10. የጨረታዉ ሳጥን በ 27 /5 /2007 ዓ/ም ከጥዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ወይም መገኘት የማይችሉ ከሆነ የተሞላ ሰነድ ካቀረቡ በሌሉበት በትግራይ አህጉረ ስብከት ልማት ማስተባበሪያ ፅ /ቤት ይክፈታል::

  11. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በክፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ::

አድራሻ 05 ቀበሌ ኮነደሚኒየም አጠገብ የኦርቶዶክስ የህፃናት ማሳደጊያ ድርጅት


 


 

መመለስ
የጨረታ ምድብ