የመቐለ እቅድና ፋይናንሰ ፅ/ፈት ቤት በከተማችን በልማታዊ ሴፍትኔት ባጀት በመጠቀም ለሚሰሩ የተለያዩ ፕሮጀክቶች የሚዉል የተለያዩ የሼድ (SMALL METALL SHADES FORLIVELY FOOD BENEFICIARIES) በሾፒንግ (ፕሪፎርማ) ኣወዳደሮ ለማሰራት ስለሚፈልግ

የፕሮፎርማ ማስታወቅያ (Shopping)

የመቐለ እቅድና ፋይናንሰ ፅ/ፈት ቤት በከተማችን በልማታዊ ሴፍትኔት ባጀት በመጠቀም ለሚሰሩ የተለያዩ ፕሮጀክቶች የሚዉል የተለያዩ የሼድ (SMALL METALL SHADES FORLIVELY FOOD BENEFICIARIES) በሾፒንግ (ፕሪፎርማ) ኣወዳደሮ ለማሰራት ስለሚፈልግ በዚ ጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉና ከታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች የምታማሉ ህጋዊ ተጫራቶች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።

CONTRACT/BID/NO ET-TIGRAY-MEKELLE-432017-CW-RFQ

ተፈላጊ መስፈርቶች

1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200.00 ብር በመክፈል ከመቸለ እቅድና ፋይናንሰ ፅ/ፈት ኣግኣዚ ኦፕሬሽን ህንፃ በመገኝዉ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 033 መግዛት ይችላሉ።

2. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ስራ ፍቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣ የኣቅራቢነት ምዝገባ ሰርቲፊኬት ፣ የሻት ምዝገባ ሰርቲፊኬት ፣ የቅርብ ወር ሻት ሪፖርት ፣ ብቃት መረጋገጫ ሴርቲፍኬት ፣ የኣነስተኛ ጥቃቅን ስራዎች በየግንባታ ስራ ደረጃ ስምንት(BC) ወይም ደረጃ 9 በጠቅላላ ስራ (GC) ደኣንት ሰርቲፍኬት ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ ።

3. የመወዳደሪያ ሀሳቡ ከ 25/06/2017 ዓ/ም እስከ 03/07/2017 ዓ/ም ሰአት3:30 ለተጫራቾች ክፍት ሁኖ የሚቆይ ሲሆን በዚህ ቀን 3:30 ተዘግቶ 4:00 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 033 ይከፈታል።

4.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና 150,000 (ብር ኣንድ መቶ ሃምሳ ሺ ብር ብቻ ) በCPO ፣ ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም የባንክ ዋስትና (Unconditional) : ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ኣለባቸው ፡፡ የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ግዜ አንስቶ ለ60ቀናት ይሆናል ።

5. የግንባታ ስራ የሚጀወረዉ ትዕዛዝ ከተሰጠበተ ቀን ጀምሮ በ90 ቀናት ዉስጥ ስራዉ የሚጠናቀቀ ሲሆን የስራ ትዕዛዝ ከተሰጠበት ዕለት ጀምሮ በሚቆጠር 90 ተከታታይ ቀናት ይሆናል።

6. በግንባታ ስራዉ ጠቅላላ ዋጋውን በቁጥርና በፊደል መፃፍ ኣለባቸው ። በቁጥር እና በፊደል በተገለፀው የዋጋ መጠን መካከል ኣለመጣጣም ካለ በፊደል የተገለፀው ተቀባይነት ይነረዋል ፡፡ በነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ካለ ነጠላ ዋጋው ተቀባይነት ይኖረዋል።

7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ፊርማቸው ፣ ቀን እና የድርጅታቸው ማህተም ማስፈር ይገባቸዋል ።

8. በጨረታዉ መሳተፈ የሚችሉት በግንባታ : ስራዉ ቢያንስ ኣንድ እና ከዚያ በላይ ተመሳሳይ ስራ የሰሩ መሆን ኣለባቸዉ፡፡

9. የክፍያ ሁኔታ በየግንባታዉ ደረጃ እየታየ የሚከፈልበት ሁኔታ ለተጠናቀቀዉ ስራ በባለሙያ በሃላፊ እየተረጋገጠ መክፈል እንዳለበት በስምምነት ላይ ሊደርስ ይችላል።

10. የመወዳደርያ ሀሳብ ማቅረብያ ቛንቛው ኣማርኛ ነው ።

11 ተጨራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ታክስን የሚያካትትና የማያካትት መሆኑን መግለፅ አለበት " ታክስን በትክክል ካልተገለፀ የቀረበው ዋጋ ታክስ እንዳካተተ ተቆጥሮ ውድድሩ ይካሄዳል ፡፡

12. በግንባታ (ኣገልግሎት) ስራዉ መሟላት ያለባቸው የስፍቶች (BOQ) ተያይዟል ፡

13. ማንኛውም ተጫራች ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰአት በፊት የዋጋ ማቅረቢያው ሰነዱን /የመወዳደርያ ሀሳብ / ማስገባት ይኖርበታል ። ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰአት በኋላ የቀረበ የዋጋ ማቅረብያ ሰነድ /የመወዳደርያ ሀሳብ ተቀባይነት የሌለው ሲሆን ኢንቨሎፑ ሳይከፈት ለተጫራቹ ተመላሽ እንዲሆን ይደረጋል።

14. የመወዳደርያ ሂሳቡ ዋጋ የሚቀርበው በኢትዮጵያ ብር ነው ፡፡

15. የጨረታ መወዳደሪያው በሚከተለው መሰረት ይሆናል ፦

15.1. በግንባታ ስራዉ ቴክኒካል መስፈርቶቹን ያማሉ መሆናቸው ይረጋገጣል።

15.2. በቀረበው ዋጋ ላይ የሂሳብ ድምር ስህተት ካለ እንዲታረም ይደረጋል ፡፡

15.3. ውድድሩ የሚካሄደው እና ዝቅተኛ ዋጋ አቅራቢ የሚለየው በታረመው ዋጋ መሰረት ይሆናል "

16. ጨረታው የቴክኒክ መስፈርቱን ካማሉት ኣቅራቢዎች መካከል ዝቅተኛ ዋጋ ላቀረበው ተጫራች አሸናፊ ይደረጋል። ከሰላምታ ጋር

መመለስ
የጨረታ ምድብ