ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የመቐለ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት የሚያገለግል የፑስተር ፓምፕ እና የተለያየ መጠን ያለው ትቦዎች ግዥ አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ስለፈለገ በጨረታው መሳተፍ ለምትፈልጉ ተጫራቾች ጥሪውን ያቀርባል።
1. የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድና የአቅራቢዎች መታወቂያ ፈቃድ ያላቸው።
2. ቫት የተመዘገቡና የመጨረሻ ወር ቫት ዲክለር ያደረገ ቲን ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ።
3. የጨረታውን ዶክመንት የማይመለስ 1000 (አንድ ሺህ) በመክፈል መቐለ ውሃ አግልግሎት ጽ/ቤት በመምጣት የጨረታውን ዶክመንት ከደጋፊ ስራ ሂደት ግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር G1–02 መግዛት ይችላሉ።
4. የጨረታ ዶክመንቱን ማስገባት የሚቻለው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 2017 ዓ/ም 4፡00 ሰዓት ወደ ጨረታ ሳጥኑ ማስገባት ይችላሉ።
5. ጨረታው የሚዘጋው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 15ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 4፡30 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ቀኑ እሁድ ወይም ህዝባዊ በዓል ከሆነ ደግሞ ቀጥሎ ባለው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች |ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
6. ሁሉም ተጫራቾች 300,000.00 /ሦስት መቶ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ፣ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ እና በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
7. ተጫራቹ ነጠላ ዋጋና የጠቅላላ ዋጋ በግልጽ ማስቀመጥ አለበት በተጨማሪም በጨረታ ዶክመንቱ ውስጥ የተዘጋጁት ፎርማት ተሞልተውና ተፈርመው መቅረብ አለባቸው።
8. በዶክመንቱ ከተሰጠው ስፔስፊኬሽን ውጪ የሚቀርብ ተቀባይነት የለውም።
9. የጨረታው አሸናፊ ውል ማስከበሪያ ካሸነፈው ዋጋ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ጋራንቲ ዋስትና የውል ማስከበሪያ (Performance bond guarantee) 10% ማስያዝ የሚችልና በ3 ቀን ውስጥ ውል አስሮ በዶክመንቱ በተጠቀሰው ቀን ንብረቱን ማስገባት የሚችል።
10. በጨረታው ሂደት ጨረታውን ለማዛባትና ለማጭበርበር የሞከረ ተጫራች ከጨረታው ውጭ እንደሚሆንና በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፍ ለማድረግ ወደ ክልሉ ፋይናንስና ፕላን ቢሮ ደብዳቤ እንደምንፅፍ ይታወቅ፡፡
11. የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ዶክመንት ተቀባይነት የለውም።
12. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተ ለ40 ተከታታይ ቀናት ብቻ ነው፡፡
13. ጽ/ቤቱ በጨረታው እንደ አስፈላጊነቱ ከእያንዳንዱ ነጠላ ዋጋ በ20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
14. የሚቀርበው የጨረታ ዶክመንት
14.1 ቴክኒካል አንድ ኦሪጅናልና ሁለት ኮፒ ሰነድ ለየብቻው በፖስታ አሽጎ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም
14.2 ፋይናንሻል አንድ ኦሪጅናል ሁለት ኮፒ ሰነድ ለየብቻው በፖስታ አሽጎ ማቅረብ የሚችል መወዳደር ይችላል።
15. ጽ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ስልክ ቁጥር 034 440 7335/091 475 5845