የብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ ራዩ/ግአስአ/ግጨ-002/2017
ራያ ዩኒቨርስቲ ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተመለከቱትን ምድብ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ምድብ | የእቃው አገልግሎት ዓይነት | የሰነድ ምድብ መግዣ ዋጋ | የጨ/ማ ዋስትና መጠን | የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ዓይነት | ጨረታው አየር ላይ የሚቆይበት | ጨረታው የሚዘጋበት ቀን | ጨረታ የሚከፈትበት ቀን |
ቀን | ሰዓት | ቀን | ሰዓት | ቀን | ሰዓት |
ምድብ 01 | ፊኖ ዱቄት | 300 | 20,000.00 | ጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በህጋዊ ባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክረዲት | ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ኛው ቀን | 11:00 | በ16ኛ ቀን | 4:00 | በ16ኛ ቀን | 4:30 |
ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት እና ተጨማሪ ዝርዝር ጉዳዮችን በጨረታ ሰነዱ ላይ በመመልከት እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል::
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ የምዝገባ ሰርተፊኬት፣ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል (ጊዜ ገደቡ ያላለፈበት) ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የሚሰጥ ታክስ ክሊራንስ፣ ጨረታ ማስከበርያ ዋስትና፣ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ EGP የተመዘገበ ወይም የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ማስረጃ፣ ሌሎች ዝርዝር የቴክኒክ መመዘኛዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ ይመልከቱ፤
- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ቀን 11፡00 ሰዓት ብቻ ራያ ዩኒቨርሲቲ ግዥ አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ ህንፃ ቁጥር 5፣ ምድር ቤት ግራውንድ በመምጣት መግዛት ይችላሉ:
- ከዋናው የጨረታ ሰነድ የሚያስፈልጉ የኮፒዎች ብዛት 2 ሲሆን በኣጠቃላይ በ3 የተለያዩ ፖስታዎች ማለትም ዋና/ኦሪጅናል የሚል ምልክት ያለው የነዚሁ ሁሉም ሰነዶች ኮፒ ደግሞ በሌላ ፖስታ ቅጂ ኮፒ የሚል ምልክት በማይለቅ ቀለም ተፅፎ ለየብቻው ታሽጎ የጨረታ ሳጥኑ ከመዘጋቱ በፊት በግዥ አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ ህንፃ ቁጥር 5 ግዥ ቡድን ምድር ቤት ግራውንድ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ::
- ጨረታ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 በተራ ቁጥር 2 በተገለፀው አድራሻ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
- ተጫራቾች አሸናፊ ለሆኑባቸው እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ዩኒቨርሲቲው ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው::
- ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስ.ቁ፡-034 877 05 01
ራያ ዩኒቨርስቲ
መመለስ