ሰሜን ሪጅን ኢትዮ ቴሌኮም ተለይተው የተቀመጡ ያገለገሉ ወንበር፣ ጠረጴዛ ፣የእንጨት በርና መስኮቶች ባሉበት ሁኔታ እና የእንጨት ምሰሶዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ይፈልጋል፡፡
  • የተለቀቀበት ቀን: ማክሰኞ ታኅሣሥ 1, 2017 (11 ቀናቶች)
  • መዝግያ ቀን: ኣርብ ታኅሣሥ 11, 2017 08:00 ከሰአት (ተዘጋ)
  • የጨረታ ማስከበርያ ዋጋ:በየሎቱ ይለያያል
  • ቦታ: መቐለ
  • የጨረታ ደኩመንት ዋጋ:100.00
  • ጨረታ ሚከፈትበት ቀንና ሰዓት: ኣርብ ታኅሣሥ 11, 2017 08:15 ከሰአት
  • ካልኦት ዝሽወጡ/ ዘገልገሉ ኣቅሑት መሸጣ/
  • Print
  • Pdf

ጨረታ ቁጥር NA, S&S /01/2017

ታህሳስ 01 ቀን 2017 ዓ.ም

ሰሜን ሪጅን ኢትዮ ቴሌኮም ተለይተው የተቀመጡ ያገለገሉ ወንበር፣ ጠረጴዛ ፣የእንጨት በርና መስኮቶች ባሉበት ሁኔታ እና የእንጨት ምሰሶዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ይፈልጋል፡፡

1. ተጨራቾች በቅድሚያ አዉቀዉ ማቅረብ ያለባቸዉ

1. ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ከ ታህሳስ 01 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 08፡00 ሰዓት ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ መቐለ ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 301 በመምጣት የማይመለስ 100.00 (ብር አንድ መቶ ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

2. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና የ 2016 ዓ.ም ታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::

3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ብር 30,000 ለወንበር፣ ጠረጴዛ የእንጨት በርና መስኮቶች ብር 20,000.00 ለእንጨት ምሰሶዎች በአጠቃላይ 50,000.00 (ሃምሳ ሺ) CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

4. የጨረታ ማስከበሪያው ከታወቀ ባንክ ተረጋግጦ በሚቀርብ ሲፒኦ (CPO) ብቻ ሊሆን ይገባል::

5. ተጫራቾች ዕቃዎችን የሚገዙበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በሚቀመጠው ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ/ፎርም በተቀመጠው መሰረት ወይም በራሳቸዉ ለወንበር፣ ጠረጴዛ ፣የእንጨት በርና መስኮቶች ባሉበት ሁኔታ ለእንጨት ምሰሶዎች የአንድ ዋጋ ከቫት (15%) በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

6. ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት የጨረታ ሰነዱን በመግዛት ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

7. አሸናፊ የሚሆነዉ ተጫራች ካሸነፈዉ ዋጋ በተጨማሪ ቫት 15% ጨምሮ ገቢ ካደረገ በኋላ በአስር /10/ የስራ ቀናት ዉስጥ ለጨረታ ተለይተዉ የተዘጋጁ ያገለገሉ ወንበር፣ ጠረጴዛ የእንጨት በርና መስኮቶች እና የእንጨት ምሰሶዎች ብቻ ማንሳት አለባቸዉ:: ሆኖም ግን በጊዜ ገደቡ ካላነሱ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኣ /cpo/ ለሪጅኑ ገቢ ተደርጎ ሪጅኑ የራሱን አማራጭ ይወስዳል ::

8. አሸናፊ ተጫራች/ ተጫራቾች በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ በራሳቸዉ ወጪ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል ፡፡

9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የገዙበትን ደረሰኝ በመያዝ ዕቃዎቹ በሚገኙበት ቦታ አዋሽ የእህል መጋዘን አጠገብ በሚገኘዉ ኢትዮቴሌኮም ጋራዥ ግቢ ዉስጥ እየቀረቡ ማየት ይችላሉ።

10. ተጨራቾች አስፈላጊዉን የመወዳደሪያ ሰነዶችን በፖስታ አሽገዉ ማስገባት ያለባቸዉ ከ ታህሳስ 01 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 08፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡ ከነዚህ ቀናትና ሰዓታት በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

11. ጨረታው ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮ ቴሌኮም ዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 301 ታሀሳስ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:15 ሰዓት ይከፈታል፡፡

12. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ያቀረቡትን ዋጋ ለመለወጥ ወይም ለማሻሻል አይችሉም፡፡

13. የጨረታው ውጤት ሳይታወቅ ውድድሩን ማቋረጥ የሚፈልግ ተጫራች ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ይደረጋል፡፡

14. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያላቀረበ ተጫራች ጨረታው በሚከፈትበት ወቅት ወዲያውኑ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡

15. ተጫራቾች ላሸነፉት ንብረት አጠቃላይ ዋጋ ቫትን ጨምሮ በኢትዮ ቴሌኮም ንግድ ባንክ አካውንት ገቢ በማድረግ ማንሳት ይጠበቅበታል

16. ተጫራቾች የማስመዘኛና የማስጫኛ እንዲሁም የሰራተኛ ወጪ በተጫራቹ የሚሸፈን መሆኑ በመገንዘብ ዋጋውን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል

17. ኢትዮ ቴሌኮም የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

መመለስ
የጨረታ ምድብ