ሱር ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ/ማሕበር በተለያዩ ፕሮጀክቶች ሊሰሩ የሚችሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች እና ተሽከርካሪዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት (መከራየት) ይፈልጋል
  • የተለቀቀበት ቀን: ቀዳሜ መስከረም 25, 2017 ( ከ 3 ወር)
  • መዝግያ ቀን: ማክሰኞ ጥቅምት 26, 2017 04:00 ጥዋት (ተዘጋ)
  • የጨረታ ማስከበርያ ዋጋ:50,000.00
  • ቦታ: መቐለ
  • የጨረታ ደኩመንት ዋጋ:100.00
  • ጨረታ ሚከፈትበት ቀንና ሰዓት: ማክሰኞ ጥቅምት 26, 2017 04:05 ጥዋት
  • መኪና ክራይ/ ማሽነሪ ክራይ/
  • Print
  • Pdf

የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ማስታወቂያ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏

ድርጅታችን ሱር ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ/ማሕበር በተለያዩ ፕሮጀክቶች ሊሰሩ የሚችሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች እና ተሽከርካሪዎች በግልፅ ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ አወዳድሮ ማሰራት (መከራየት) ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ው ላይ መወዳደር የምትፈልጉ ደምበኞች (ተጫራቾች) በጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ው ላይ ለመሳተፍ ልታሟሏቸው የሚገባችሁ ዝርዝር ሁኔታዎች፡-

  1. የማሽኑ ወይም የተሽከርካሪው የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር (ሊብሬ)
  2. ተጫራቾች የ 2017 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርቲፊኬት፣ እና ሌሎች መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ፤
  3. ተጫራቾች ለጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ የተዘጋጀ ዝርዝር የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ሰነድ ከ23/01/2017 ዓ.ም ጀምሮ በስራ ሰዓት‍‍‍‍‌‍‌‍‌‌‌‍‍‍‌‍ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) እየከፈሉ በአዲስ አበባ ቦሌ ሜጋ ህንፃ አጠገብ ከሚገኘው ዋና መስሪያ ቤታችን፤ በመቀሌ ላጪ ከሚገኘው ቅርንጫፍ መስሪያ ቤታችን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ከድርጅታችን የተሰጣቸው ኦርጅናል ፎርም ብቻ ተጠቅመው ያለ ስርዝ ድልዝ ቫት ሳይጨምር (ከቫት በፊት) ለእያንዳንዱ አይነት ማሽን ወይ ተሽከርካሪ በጥንቃቄ ነጠላ ዋጋ ሞልተው፣ ፈርመው እና ማህተም አድርገው በታሸገ ኤንቨሎፕ እንዲልኩልን ወይም ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ው በሚከፈትበት ቀን እና ሰዓት በአካል ይዘው መምጣት አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ከመከፈቱ በፊት የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ማስከበርያ ብር 50,000.00 ( ሃምሳ ሺህ) ሲፒኦ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  6. ለድርጅታችን ስራ የሚውል የነዳጅ ወጪው በድርጅታችን የሚሸፈን ይሆናል፡፡
  7. የማጓጓዣ ወጪን (ዋጋ) በሚመለከት ወደ ፕሮጀክት ለማጓጓዝ የሚያስፈልግ ወጪ በድርጅታችን የሚሸፈን ሲሆን ከፕሮጀክት ለማውጣት (ለመመለስ) የሚያስፈልግ ወጪ በአከራይ (በደምበኛ የሚሽፈን ይሆናል፡፡
  8. አንድ ተጫራች (ደምበኛ ከተጠቀሱት አይነት ማሽኖች እና ተሽከርካሪዎች በፈለገው አይነት ማሽን ተሽከርካሪ ብቻ የመጫረት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ው የሚከፈትበት ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 25/02/2017 ዓ.ም ሰኞ ከጠዋቱ 4:00 (አራት ሰአት) አዲስ አባባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት 16ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1601 እንዲሁም በመቀሌ ላጪ በሚገኝ ቅርንጫፍ መስሪያቤታችን ሁኖ ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ው ሲከፈት የተገኘም ሆነ ያልተገኘ ደምበኛ በውጤቱ ተገዢ ይሆናል፡፡
  10. ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ውን ያሸነፈው ተወዳዳሪ ተጫራች ያሸነፈው ብዛት እና ዓይነት ማሽነሪ እና ተሽከርካሪ ሊያቀርብ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ በአምስት ተከታታይ ቀን ውስጥ ላሸነፈበት ዓይነት እና ብዛት ማሽነሪ እና ተሽከርካሪ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ውን ያሸነፈው ደምበኛ ተጫራች ከተነገረበት ቀን ጀምሮ በአምስት ተከታታይ ቀን የሚፈለገው አይነት እና ብዛት ማሽነሪ እና ተሽከርካሪ ማቅረብ ካልቻለ፤ እሱ ባሸነፈበት ዋጋ ሌሎች ደምበኞች አቅራቢዎች ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡
  11. ድርጅታችን የተሻለ ኣማራጭ ካገኘ ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 911 904 34/0914 297 662 ወይ በአካል መጠየቅ ይችላሉ

ሱር ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ/ማሕበር

መመለስ
የጨረታ ምድብ