1 በዘርፉ የታደሰ የዘመኑ ንግድ ፈቃድ ያለዉና ኮፒ ማቅረብ የሚችል
2 የአቅራቢዎች ምዝጋበ ያለዉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ እና ግብር ስለመከፈሉ
የምስክር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ የሚችል
3 የጨረታ ማስከበሪያ 15.000 ብር በመቐለ ዩኒቨርስቲ የኢትዩጰያ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መቐለ ስም ስፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል
4 ተጫራቾች ኢንስቲትዩት ባቀረበዉ ፎርም በድርጅታቸዉ ስም ቃለ መሃላ ፈርመዉ ማቅረብ ይኖርባቸዋል
5 ጨረታዉ በሁለት ኢንቨሎፕ ታሽጎ የሚቀርብ ሲሆን ዋናዉና ቅጂ ሰነድ በድርጅቱ ስልጣን ባለዉ አካል ፊርማና ማህተም ሊኖረዉ ይገባል የንግድ ፈቃድ ኮፒ ቃለ ማሃላ የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት ስፒኦ ና ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶች በኦርጅናል ዶክመንት መግባት አለበት
6 ተጫራቾች በሚቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ስመቸዉን ፊርማቸዉና ኣድራሻቸዉን ማስፈር አለባቸዉ
7 ጨረታዉ ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ዉጭ እንደሚደረጉና ለወደፊትም ጨረታ እንዳይሳተፉ ይደረጋል
8 ጨረታ ከተከፈተ በኃላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወደደሪያ ሓሳብ ላይ ለዉጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራሳቸዉን ማግለል አይችሉም
9 አሸናፊ ድርጅትቶች ያሸነፈዉ ፋት እቃ በራሳቸዉ ወጪና ትራንስፖርት እቃዎች ለኢትዩጰያ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መቐለ ማድረስ አለበት
10 ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ የማብራሪያ ወይም የማሻሻያ ጥያቄ ከተወሰነዉ ጊዜ ገደብ በፊት በስልክ ቁጥር 0344 412801 መጠየቅ ይችላሉ
11 ተጫራቾች በጨረታ አፈፃፀም ሂደት ቅሬታ ካላቸዉ አቤቱታ የማቅረብ መብት አላቸዉ
12 ተመሳሳይ ዋጋ እና ስፐስፊኬሽን ያቀረቡ ተጫራቾች እንደገና ዋጋ እንዲያቀርቡ ይደረጋል
13 ተጫራቾች በኢንስቲትዩቱ የቀረበዉ ናሙና በአካል በመቅረብ ጨረታዉ ከመከፈቱ በፊት ማየት አለባቸዉ
14 ተጫራቾች ከኢንስቲትዩቱ አስፈላጊዉን የተለያዩ ሃንድ አዉትና መፅሓፍቶች በመዉሰድ ኮፒ አድረገዉ በራሳቸዉ ወጪ ማቅረብ አለባቸዉ
15 ተጫራቾች ኢንስቲትዩቱ በሚጠየቅዉ የኮፒ ብዛት በየወቅቱ ማቅረብ አለባቸዉ
16 ጨረታዉ በአየር የሚቁይበት ጊዜ ከሚያዝያ 03/08/2008 ዓ/ም እስከ ሚያዝያ 17/08/2008 ዓም ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋበት ቀን በ 17/08/2008 ዓ/ም ከጥዋቱ 3:30 ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ 4:00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በመቐለ ዩኒቨርስቲ የኢትዩጰያ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መቐለ ቢሮ ቁጥር 304 ዋናዉ ግቢ ይከፈታል ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸዉ ምርጫ ጨረታዉን በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸዉ የጨረታዉን መክፈት አይስተጓጉልም
17 የጨረታ ሰነዱ ከንግድ ምክር ቤት ወይም ኢንስቲትዩት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በነፃ መዉሰድ ይችላሉ
18 በፊደራል መንግስት የግዥ አፈፃፀም መመርያ መሰረት ኢንስቲትዩት አስፈላጊ ሁኖ ካገኘዉ 25% መጨመር መቀነስ ይችላል
19 ያንዱ ዋጋ ሲሞላ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት
20 ኢንስቲትዩቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ
መመለስ