የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ማይጨው ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚሆን ቤት መከራየት ይፈልጋል
  • የተለቀቀበት ቀን: ሮብ ሐምሌ 17, 2016 ( ከ 5 ወር)
  • መዝግያ ቀን: ሮብ ነሐሴ 1, 2016 04:00 ጥዋት (ተዘጋ)
  • የጨረታ ማስከበርያ ዋጋ:
  • ቦታ: ማይጨዉ
  • የጨረታ ደኩመንት ዋጋ:
  • ጨረታ ሚከፈትበት ቀንና ሰዓት: ሮብ ነሐሴ 1, 2016 04:30 ጥዋት
  • ገዛ/ህንፃ ክራይ/
  • Print
  • Pdf

ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ቤት ኪራይ

ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ማስታወቂያ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏

የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ማይጨው ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚሆን ቤት መከራየት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፡-

1. ከ14 ክፍል በላይ ብዛት ያለው እና ለቢሮ አመቺ የሆነ፤

2. አማካይ የአንድ ክፍል ስፋት ቢያንስ 4*3 ሜ እና ከዚያ በላይ ስፋት ያለው፤

3. የራሱ ግቢ ያለው ፣ለጥበቃ ምቹ የሆነ እና አጠቃላይ 460 ካሬ እና ከዛ በላይ የሆነ፤

4. የወንዶች እና የሴቶች መጸዳጃ ቤት እና ሻወር ያለው፤

5. ከመሃል ከተማ እምብዛም ያልራቀ እና ለህዝብ ትራንስፖርት ቅርብ እና አመቺ የሆነ፤

6. አካባቢው ከማንኛውም ድምጽ ብክለት የራቀ፤

7. ቢያንስ ለ5 አመታት ውል ለማሰር ፍላጎት ያለው፤

8. የቤት ባለቤትነት ማረጋገጫ ማስረጃ የሚያቀርብ ፤

9. የ2016 በጀት አመት ግብር የከፈለ እና ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው።

ተጫራቾች የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ውን ሰነድ ማስታወቂያ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮእስከ 16ኛው ቀን ድረስ የመንግስት ሠራተኞች ማኀበራዊ ዋስትና አስተዳደር ማይጨው ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመሄድ እና ሰነዱን መውሰድ የሚችሉ ሲሆን የሚጫረቱበትን የአንድ ካሬ ዋጋ ከጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ሰነዱ ጋር በዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው ለጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ማይጨው ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቢሮ ማስገባት አለባቸው። ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ው አየር ላይ በዋለበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት‍‍‍‍‌‍‌‍‌‌‌‍‍‍‌‍ ተዘግቶ የሚከፈተውም በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቻው በተገኙበት ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ማይጨው ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቢሮ ነው። 16ኛው ቀን የእረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ው ከላይ በተገለጸው ሰዓት በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል።

አስተዳደሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር ፡- 034 777 0289

የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ማይጨው ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

መመለስ
የጨረታ ምድብ