የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐለ ዲስትሪክት በዋስትና የያዘውን የሆቴል ድርጅት ህንፃዎች እና የሆቴል መገልገያ ቁሳቁሶች በሐራጅ ለመሸጥ ይፈልጋል
  • የተለቀቀበት ቀን: ኣርብ ግንቦት 16, 2016 ( ከ 7 ወር)
  • መዝግያ ቀን: ማክሰኞ ሰኔ 18, 2016 05:00 ጥዋት (ተዘጋ)
  • የጨረታ ማስከበርያ ዋጋ:25%
  • ቦታ: መቐለ
  • የጨረታ ደኩመንት ዋጋ:
  • ጨረታ ሚከፈትበት ቀንና ሰዓት: ማክሰኞ ሰኔ 18, 2016 07:00 ከሰአት
  • ናይ ገዛ/ህንፃ ሓራጅ/ ገዛ/ህንፃ ምሻጥ/
  • Print
  • Pdf

የሐራጅ‍‍‍‍‌‍‌‍‌‌‌‍‍‍‌‍ ማስታወቂያ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐለ ዲስትሪክት ለአቶ አታኽልቲ ሐጎስ ገ/ዝጊ ለሰጠው ብድር አመላለስ በዋስትና የያዘውንና ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/11 በተሰጠው ስልጣን መሠረት በሐራጅ ለመሸጥ ይፈልጋል።

የተበዳሪው/ መያዣ ሰጪው ሰም

የመያዣ ንብረቱ አድራሻ

ለሐራጅ የቀረበ ንብረት ዓይነትና ዝርዝር

የቦታው ስፋት በካ/ሜ

የሐራጁ መነሻ ዋጋ /በብር/

የሐራጁ ደረጃ

ሐራጅ የሚካሄድበት ቀን እና ሰዓት‍‍‍‍‌‍‌‍‌‌‌‍‍‍‌‍

አታኽልቲ ሓጎስ ገ/ዝጊ

በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን አክሱም ከተማ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር 7299/ድ/2016 የሆነ

የሆቴል ድርጅት ህንፃዎች እና የሆቴል መገልገያ ቁሳቁሶች

4552.74

27,806,388.86 /ሃያ ሰባት ሚሊዮን | ስምንት መቶ ስድስት ሺህ ሦስት መቶ ሰማንያ ስምንት ብር ከ86 ሣንቲም/

አንደኛ

ሰኔ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 -7፡00

ማሳሰቢያ

  1. ተጫራቾች ንብረቱን ለመጎብኘት ከፈለጉ አስቀድመው ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በመያዝ ከሐራጁ ቀን በፊት ንብረቱን መጎብኘት ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ 25% (ሃያ አምስት በመቶ) በባንከ ማዘዣ ሲፒኦ (CPO) ብቻ አሰርተው ከሐራጁ ቀን በፊት ማስያዝ ወይም ሐራጅ በሚካሄድበት ዕለት ሐራጁ ከመከፈቱ በፊት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል። በሐራጁ የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
  3. በሐራጁ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ሐራጁ ከመጀመሩ በፊት ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት በፊት ባለው ጊዜ ሐራጁ በሚካሄድበት ቦታ በህጋዊ ወኪል በኩል ቀርቦ መመዝገብ ይኖርበታል።
  4. ሐራጁ ከላይ በተገለፀው ቀንና ሰዓት ተበዳሪው መያዣ ሰጪው ወይም ህጋዊ ወኪላቸው፣ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት በፕሮጀክቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይካሄዳል። በጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ቀንና ሰዓት መያዣ ሰጪው ወይም ህጋዊ ወኪላቸው እና ታዛቢዎች ባይገኙም ሐራጁ ይካሄዳል።
  5. በሐራጁ የተሻለ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ማሸነፉን የሚገልፅ ደብዳቤ ከባንኩ ሲደርሰው አሸናፊ ይሆናል።
  6. ሐራጁን ያሸነፈ ተጫራች አሸናፊ መሆኑ በፅሁፍ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ዋና በ15 ተከታታይ ቀናት ጊዜ ውስጥ ለባንኩ አጠቃሎ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል። በተገለፀው ጊዜ ውስጥ አሽናፊው ገንዘቡን ገቢ ካላደረገ ሐራጁ ይሰረዛል፤ ያስያዘው ገንዘብም ለባንኩ ገቢ ይሆናል። ሐራጁን ያሸነፈ ተጫራች ያሸነፈበትን ገንዘብ በጥሬ ገንዘብ ለባንኩ መክፈል ይኖርበታል። ሆኖም አሸናፊው በባንኩ የብድር ፖሊሲ መሠረት አስፈላጊውን መስፈርቶች ካሟላና የፕሮጀክቱን ሥራ የሚያስቀጥል ከሆነ ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት መጠየቅ ይችላል።
  7. የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው ተሽከርካሪ እና ማሽነሪዎች በተመለከተ ገዢው የቀረጥ ነፃ መብት ሊኖረው ይገባል ወይም በንብረቶቹ ላይ በመንግሥት የሚፈለገውን ቀረጥና ታክስ መክፈል ይኖርበታል።
  8. የንብረቱ ስም ለንብረቱ ገዢ እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል። ገዢው ጉዳዩን ተከታትሎ ያስፈፅማል።
  9. ሐራጁ ከመካሄዱ በፊትም ሆነ ከተካሄደ በኋላ ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ወይም ብድሩ ከተከፈለ ሐራጁን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. ሐራጁን ያሸነፈ ተጫራች የሽያጩን 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎች የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ይከፍላል።
  11. ለተጨማሪ መረጃ መቐለ ዲስትሪክት ሎን ዎርክአውት ዲቪዥን በኣካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 034-440-7439 ፤ 034-441-9016 ማግኘት ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐስ ዲስትሪክት

መመለስ
የጨረታ ምድብ