ኩባንያችን መስፍን ኢንዳስትሪያል ኢንጂነሪንግ ኃላ.የተወየግል ኩባንያ (FSWEI ኢንድስትሪ) ከታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች እንድትሳተፉ ኩባንያችን ይጋብዛል::
  • የተለቀቀበት ቀን: ሮብ ግንቦት 7, 2016 ( ከ 8 ወር)
  • መዝግያ ቀን: ሰኞ ግንቦት 12, 2016 08:00 ከሰአት (ተዘጋ)
  • የጨረታ ማስከበርያ ዋጋ:50,000.00
  • ቦታ: መቐለ
  • የጨረታ ደኩመንት ዋጋ:
  • ጨረታ ሚከፈትበት ቀንና ሰዓት: ሰኞ ግንቦት 12, 2016 08:30 ከሰአት
  • ኮንስትራክሽን ማሽነሪን ኣቁሑትን/
  • Print
  • Pdf

የጨረታ ማስታወቂያ

ኩባንያችን መስፍን ኢንዳስትሪያል ኢንጂነሪንግ ኃላ.የተወየግል ኩባንያ (FSWEI ኢንድስትሪ) ከታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች እንድትሳተፉ ኩባንያችን ይጋብዛል::

ተ.ቁየዕቃው ዓይነት ዝርዝርመለኪያብዛትማብራርያ
01Manhole Cover with out ring Ø500 mm (Normic type)pcs30

የጨረታ መስፈርት

1. ተጫራቾች በዘርፉ የ2016 ዓ/ም የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የግብር ከ ከፋይ መለያ ቁጥር እና የወሩ ቫት ማሳወቅያ ፎቶ ኮፒ በማያያዝ ከጨረታው ዝርዝር (ሰነድ)ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል::

2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የወሩ ቫት

ማሳወቅያ ፎቶ ኮፒ የማይመለስ እና ኦርጅናል የሚመለስ በመያዝ የጨረታ ሰነድ ከቀን 14/05/2024 እ.ኤአ ጀምሮ እስከ 20/05/2024 እ.ኤአ መቐለ ላጪ ቅርንጫፍ  ኢንድስትሪ በስራ ሰኣት መወሰድ ይኖርባቸዋል::

3. ጨረታው 20/05/2024 እ.ኤ.አ ከቀኑ 8:00 ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ከሰኣት 8:30 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት መቐለ ዋና መስርያ ቤት በሚገኝ FSWEI ኢንድስትሪ ሳፕላይ ቢሮ የሚከፈት ሲሆን ሰነዳቸው የተሟላ ከሆነ ባይገኙም የጨረታ ሰነዱ ይከፈታል::

4. አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን አሸንፈው ውል ካሰሩበት ቀን ጀምሮ በ 5 ቀናት ውስጥ እቃው ማስረከብ አለባቸው::ይህ ካልሆነ ግን ለውል ማስከበርያ ያስያዙት ብር ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ድርጅቱ ሌላ አማራጭ ይወስዳል::

5. ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ቫት(VAT) ጨምሮ መሆኑና አለመሆኑን በግልፅ መጠቀስ አለበት:: ይህ ካልሆነ ግን ያስገቡት ዋጋ ቫት እንደሚያካትት ተቆጥሮ ይወሰዳል::

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ ) ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በታሸገ ፖስታ ከጨረታው ጋር ማስገባት አለባቸው::በፖስታ ያልታሸገ ሲፒኦ ተቀባይነት የለውም::

7. አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተነገራቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋ ቫት ጨምሮ 10% የውል ማስከበርያ የባንክ ዋስትና (Unconditional bank guarantee) በማሰራት ከኩባንያችን ጋር ውል መፈራረም አለባቸው:: ይህ ካልሆነ ግን ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዙት ብር ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ድርጅቱ ሌላ አማራጭ ይወስዳል::

8. ተጫራቾች በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ተመስርተው ዋጋ ማስገባት አይፈቀድም::

9. ተጫራቾች ይህን ጨረታ ካሸነፉ ለሌላ ሶስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት አይችሉም::

10. ተጫራቾች ተጫርተው ያሸነፉት እቃ መቐለ ዋና መስርያ ቤት ድረስ መጥተው ማስረከብ አለባቸው:: ክፍያ በተመለከተ ያቀረቡት እቃ ድርጅታችን ጥራት ቁጥጥር ባለሙያ ተፈትሾ ተቀባይነት ካገኘ በኃላ በ10 ቀናት ውስጥ የሚፈፀም ይሆናል::

11. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::

መመለስ
የጨረታ ምድብ