የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አዲ-ግራት መንገድ ጥገና ዲስትሪከት የተለያዩ የሰራተኞች ጥቅማ ጥቅም/አልባሳት፣ ጫማ ፣ የመፀዳጃ ወረቀት ፣ የልብስ ሳሙና ፣ የገላ ሳሙና/ እንዲሁም ኮምፒውተርና ላፕቶፖች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ብቁ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ድርጅቶች በኢትዮጵያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በመንግስት ዕቃና አገልግሎት አቅራቢነት በኤጀንሲው ደህረ ገፅ Website/ የተመዘገቡ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በጨረታ ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቶች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ከሚፈልገው ግዥ የተዛደ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፊኬት እና በጨረታው ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢዎች ቢሮ ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ በማቅረብ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ሜክሲኮ ከሚገኘው የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና መ/ቤት /አዲስ አበባ/ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ከፍት ነው፡፡ የጨረታ ሰነድ የተዘጋጀው በአማርኛ ቋንቋ ነው፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ጨረታ ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዶች ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልከ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸው ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ አዲስ አበባ ዋና መ/ቤት ግዥ ቡድን ገቢ የሚያደርጉበት የመጨረሻ ቀን ታህሳስ 02/2016 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውን በተገኙበት ታህሳስ 02/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት አ/አ ዋና መ/ቤት በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የበለጠ መረጃ- ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
ሞባይል፡- 09-29-72-66-38/09-48-50-93-27 ወይም 09-38-17-64-17
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር
የአዲግራት መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
መመለስ