- ጨረታዉ በኣዲስ ዘመን ጋዜጣ የወጣበት ቀን : 21/9/2012
ጨረታዉ የሚዘጋበት ቀን: በ16 ቀን ከጠዋት 3:00 ሰዓት
ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን: በ16 ቀን ከጠዋት 3:30
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ ተጫራቾች የ2012 ዒ.ም የታደሰ/አዲስ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት (TIN No.) ማቅረብ የሚችሉ:: - ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ከሚያቀርቡ ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመከፈቱ በፊት ወይም ከጨረታው ሰነድ ጋር በወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት ስም ማቅረብ ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል ከወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት ከማይ ጋባ ከተማ በፕሮጀክቱ አቅርቦትና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት መምርያ በግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ወይም ከመቀሌ ከተማ የትግራይ ልማት ማህበር ከሚገኘው የፕሮጀክቱ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 375 የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለጽ በታሸገ ኤንቨሎፕ በፕሮጀክቱ አቅርቦትና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት መምርያ በግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ::
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚህ ቀን ጠዋት 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት በአቅርቦትና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት መምርያ ይከፈታል፡፡
- ፕሮጀክቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡ ፡ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቀጥር፡የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት ሲቁ፡- 0914001262/ 0929184332/ 09147236-49
- የመቀሌ ላይዘን ኦፊስ ስቁ፡- 0344416452 /0918445826 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት
መመለስ