በሃገር መከላከያ ሚኒስቴር በሰሜን ዕዝ የ5ኛ ሜ/ድ ክ/ጦር መምሪያ በ2012 በጀት ዓመት ለክ/ጦራችን ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነት ያገለገሉ የምግብ ማብሰያና መገልገያ እቃዎችና ፕላስቲክ በርሜሎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
  • የተለቀቀበት ቀን: ቀዳሜ ታኅሣሥ 25, 2012 (ከ 5 ዓመታት)
  • መዝግያ ቀን: ማክሰኞ ጥር 12, 2012 08:00 ከሰአት (ተዘጋ)
  • የጨረታ ማስከበርያ ዋጋ:50000.00
  • ቦታ: መቐለ
  • የጨረታ ደኩመንት ዋጋ:50.00
  • ጨረታ ሚከፈትበት ቀንና ሰዓት: ማክሰኞ ጥር 12, 2012 08:15 ከሰአት
  • ካልኦት ዝሽወጡ/ ዘገልገሉ ኣቅሑት መሸጣ/
  • Print
  • Pdf
  • የተለያዩ አይነት ያገለገሉ የምግብ ማብሰያና መገልገያ እቃዎችና
  • ፕላስቲክ በርሜሎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች በሙሉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ 

መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የማስረጃቸውን ፎቶ ኮፒ በማቅረብ የዕቃዎችን ዝርዝር የያዙ ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00 (ሃምሳ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በ5ኛ ሜ/ድ ክ/ጦር ዳንሻ ወ/ዊ ካምፕ ግዥ ክፍል ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ለተሸናፊው  ተመላሽ  የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ ብ 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር)  በባንክ   በተረጋገጠ cpo ወይም በካሽ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራቾች የእያንዳንዱ የዕቃ ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ ጥር 12 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ሰነዱን ከገዙበት ቢሮ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

ጨረታው 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ5ኛ ሜ/ድ ክ/ ጦር ወ/ዊ መዝናኛ ክበብ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለበለጠ መረጃ

በስልክ ቁጥር 0930962249/0913133315 ይደውሉ፡፡

በሰሜን ዕዝ የ5ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር መምሪያ

መመለስ
የጨረታ ምድብ