ቤት ፅሕፈት ኮ/መ/ት

በትግራይ ክልል የኮንስትራክሽን መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ዳይሬክቶሬት ሕንፃ ዲዛይንና ኮንስትራክሽን በ2011 በጀት ዓመት ሑመራ ከተማ ሆስፒታል ህንፃ ፕሮጀክት ግንባታ ለማካሄድ በደረጃ BC-5/GC-6 እና ከዛ በላይ ለሆኑ ኮንትራክተሮች አጫርቶ ለመስራት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።

  • የ2010 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የቫት ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የባለፈው ወር የቫት ዲክላሬሽን፣ የቲን ምዝገባ፣ የኮንትራክተር ምዝገባ ካርድ ማስረጃዎችን ማቅረብ የሚችሉ።
  • የጨረታ ማስከበሪያ በህግ ከታወቀ ባንክ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና (unconditional bank guarantee) ወይም የገንዘብ ክፍያ ማዘዣ CPO ብር 400,000 /አራት መቶ ሺ ብር/ ማቅረብ አለባቸው።
  • መስፈርቶቹን የሚያሟሉ ሁሉም ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 30 /ሰላሳ/ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከዳይሬክቶሬቱ መግዛት ይችላሉ።
  • ለተጨማሪ ማብራሪያ ወደ ትግራይ ክልል ኮንስትራክሽን መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ዳይሬክቶሬት ህንፃ ዲዛይንና ኮንስትራክሽን ቢሮ ቁጥር 191 በአካል በመቅረብ ወይም በ0344408773 የስልክ መስመር በመደወል መጠየቅ ይቻላል።