በዚሁ መሰረት በጨረታዉ መወዳደር የሚፈልጉ ማንኛዉም ህጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች በሟሟላት ማቅረብ ይኖርባቸዋል
1 ተወዳዳሪዎች
- በዘረፉ የ2007/8 ዓ/ም የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቅድ ያላችሁ
- VAT ተመዝጋቢዎች መሆናቸዉ ማስረጃ የሚቀርቡ
- የጥቅምት /ሕዳር ወር የቫት ዲክለራስዩን ያላቸዉና ማስረጃ ሚያቀርቡ
- ቲን ናምበር ያላቸዉና ማስረጃ የሚቀርቡ
- በክልል ፋይናንስ ይሁን በፌደራል የመንግስት ግዢ በኣቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የ2007/8 ዓ/ም የታደሰ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት የሚቀርቡ
2 ተጫራቾች የጨረታዉ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ
- ለሞተር ሳይክል ብር ብር 30,000 /ሰላሳ ሺ ብር/
- ለስተሽነሪ ጠቃቅን እቃዎች ብር 4000 /አራት ሺ ብር/
- ለመኪና ጋራዥ ብር 2000 /ሁለት ሺ ብር/
- ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ብር 5000 /አምስት ሺ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ስፒኦ በጥሬ ገንዘብ ወይም ሰርቲፋይድ ቼክ በትግራይ ክልል የገጠር መሬት አካባቢ ኣጠቃቀምና ኣስተዳደር ኤጄንሲ ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር መመርያ የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 17 በመዉሰድ ዋጋ ማቅረብያ ሰነዳቸዉን በስም በታሸጉ ኢንቨሎፕ ይህ ማስታወቅያ ከወጣበት ከ 26/03/2008 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 12/04/2008 ድረስ በስራ ሰዓት ለክልሉ የገጠር ልማት መሬት አከባቢ ጥበቃ አጠቃቀምና ኣስተዳደር ኤጄንሲ ፓሳቁ 1234 በአድራሻ በመለክ ወይም በግንባር በመቅረብ በቢሮ ቁጥር 17 ለዚሁ በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላሉ
3 ጨረታዉ በ17ኛዉ ቀን በ 12/4/2008 ዓ/ም በ 8:00 ሰዓት ከታሸገ በኃላ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪቻቸዉ በተገኙበት የተሻለ ቢሆን ባይገኝም በ 8:30 ሰዓት በክልሉ የገጠር መሬት የኣከባቢ ጥበቃ አጠቃቀምና ኣስተዳደር ኤጄንሲ ይከፈታል
4 ኣሸናፊዎች ላሸነፉት ዋጋ ዉል የማሰር /የመግባት/ ግዴታ አለለባቸዉ በገቡት መሰረትም ይፈፅማሉ በገቡት ዉል ሳይፈፅሙ በቀሩ በእያንዳንዱ ቀን ካሳያዙት የዉል ማስረከቢያ ጠቅላላ ዋጋ 0.1% በመቀጣት ገቢ እንዲያደርጉ ይደረጋል ወይም በህግ ይቀጣል
5 ተጫራቾች በቀረበዉ ጨረታ ሰነድ አስተያየት /ጥያቄ ከለዎት ከጨረታ መክፍቻዉ ከ5 ቀን በፊት ማቅረብ ይችላሉ በጨረታ ሰነድ ስርዝ ወይ ድልዝ ካለበት ተቀባይነት ኣይኖረዉም ከተጠቀሰዉ ቀን በኃላ ለሚመጣ ጥያቄ ኤጄንሲዉ መልስ ለመስጠት ኣይገደድም
6 የሞተር ሳይክልና የመኪና ጥገና ጋራዥ ተወዳዳሪዎች ፋይናንሻል ዶክመንት ለብቻዉ ቴክኒካል ዶክመንት ለብቻዉ አሽገዉ ማቅረብ አለባቸዉ
7 ቢሮዉ የተሻለ አማረጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ
8 ለተጨማሪ ማብራርያ በስልክ ቁጥር 0344417104 ደዉለዉ መጠየቅ ይቻላል
ፋክስ ቁጥር 0344 411697