ጨረታዉ በጋዜጣ የወጣበት ቀን : 14/4/2010
1 በዘረፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ: የቫት ምዝገባ ሰርተፊኬት: የግብርር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የአቅራቢ ምዝገባ ሰርተፊኬት ሊብሬ ኢንሹራንስ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
2 በቀረበዉ ዝርዝር የቴክኒክ መስፈርት ማሟላት የሚችል
3 ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በባንክ የተመሰከረለት CPO /ስፒኦ/ ወይም የባንክ ዋስትና በመቐለ ዩኒቨርስቲ ስም ማስያዝ የሚችል
ተቁ | ምድብ | የጨረታዉ አይነት | ስፒኦ |
4 | ሎት 1 | እንዳስትርያል ኣዉቶሜሽን የስልጠና እቃዎች | ብር 200,000.00 |
5 | ሎት 2 | የቢሮ እቃዎች ፈረኒቸር | ብር 50,000.00 |
4 ማንኛዉም ተጫራች 100.00 /ኣንድ መቶ ብር/ በመክፈል ለዚሁ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሰነድÂ ከመቀሌ ዩኒቨርስቲ ዋናዉ ግቢ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳ/ጽ/ቤት መዉሰድ ይችላል
5 ጨረታዉ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21 ኛዉ ቀን 3:30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይችላሉ
6 ጨረታ ከወጣበት በ21ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ በተመሰሳይ ቀን ልክ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በግልፅ ይከፈታል 21ኛዉ ቀን በዓል ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ ይከፈታል
7 በጨረታ አሸንፎ በወቅቱ ወል ለማያስር የጨረታ አሸናፊ ያስያዘዉ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ (CPO) አይመለስለትም
8 ዩኒቨርስቲዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብተ የተጠበቀ ነዉ
ለበለጠ መብራሪያ በስልክ ቁጥር 0348 40 99 52 ደዉለዉÂ ማነጋገር ይቻላል
መቐለ ዩኒቨርስቲዉ የመቐለ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ኣይናለም ግቢ