የጨረታ ማስታወቂያ

የትግራይ ክልል ምክር ቤት ፅ /ቤት ለ 2007 የበጀት ዓመት ኣገልግሎት የሚዉል ከዚሀ በታች የቀረበዉ እቃ በግልፅ ጨረታ ኣወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

1 ቆሚ የቢሮ እና የኣዳራሽ እቃዎች ማለትም የቢሮ ጠረጽዛዎች ተሽከርካሪ ወንበሮች የእንግዳ ወንበሮችና ሸልፍ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::

ስለዚህ በዘርፉ የተሰማሩ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሞሉ ድርጅቶች ኣወዳድሮ ማጫረት ይፈልጋል::

  1. በተሰጠዉ የስራ ዘርፍ::

  2. ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያለዉ የዘመኑ ግብር የከፈሉና ኮፒዉን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ::

  3. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀትና የግብር መለያ ቁጥር / ቲን/ ያለዉና ኮፒዉን ማስረጃ ማቅረብ የሚቸሉ

  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ለመሆናቸዉ ማሰረጃ ኮፒዉን ማቅረብ የሚቸሉ

  5. ተጫራቾች የጨረታዉን ሰነደ ከትግራይ ክልል ምክር ቤት ፅህፈት ቤት ህንፃ ground ቢሮ ቁጥር የስራ ሂደት ፋይናንስ ግዥና ንብረተ ኣሰተዳደር በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 /መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል መዉሰድ አለባቸዉ ይኸዉም ከቀን 10 /05/ 2007 ዓም ጀምሮ እስከ 09 /06 /2007 በስራ ሰዓተ ይሆናል::

  6. የጨረታዉ ማሰከበሪያ /bid bond/ ብር 30 ,000. 00 ሰላሳ ሺ ብር ጨረታዉ ከመከፈቱ በፊት ከዋጋዉ ማቅበብያ ጋር በባንክ በተረጋገጠ: /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላየ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /ጋራንት / ከመጫረቻ ሰነዳቻቸዉ ማቅረብ ኣለባቸዉ::

  7. በወቅቱ ቫተ ዲክለር የተደረገበት ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ::

  8. ከላይ የተዘረዘሩት የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ : የአቅራቢነት : ቲን : ቫት ሰርትፍኬት : ቫት ዲክለር የተረገበት:/ CPO/ ሲፒኦ እና ሌሎች ከቴክኒካል ኦርጅናል ደኩመንተ ጋር ማስገባት አለባቸዉ:;

  9. መ ቤቱ በጨረታ ካቀረበዉ ብዛት እስከ 20 % ድረስ የመጨመር ወይም የመቀነስ ምብቱ የተጠበቀ ነዉ

  10. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በኣዲስ ዘመን 74ኛ ዓመት ቁጥር 130 ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 30 ቀናተ ጨረታ ሰነድ በመግዛት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፐ ዉስጥ በማድረግ በትገራይ ክልል ምክር ቤት ፅህፈተ ቤት ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር ለዚሁ በተገዛጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት የሚችሉ ሲሆኑ ጨረታዉ በ 30 ኛ ቀን ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን 9:00 ሰዓት ላየ ተጫራቸች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ወይም ባይገኙመ ይከፈታል::

  11. ጨረታዉ በ 09/ 06/ 2007 ዓ/ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን 9:00 ሰዓት ላይ ተጫራቸች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ወይም ባይገኙመ ይከፈታል::

  12. የጨረታ ዋጋዉ ጨረታ ከተከፈተበት ግዜ ጀምሮ ለ 45 ቀናት ፀንቶ ይቆያል::

  13. አሸናፊዉ ተጫራቾች የዉል ማስከበሪያ 10 % በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ በድርጅቱ ስም/ ትግራይ ክልል ምክር ቤት/ ማስያዝ አለባቸዉ::

  14. ተጫራቾች የጨረታዉ ቴክኒካል ፋይናንሻል ደኩመንት ኣንድ /1 / ኦርጅናልና ኣንድ /1 / ኮፒ ለየብቻዉ ማቅረብ አለባቸዉ::

  15. አሸናፊዉ ተጫራቾች ቢያንስ የአንድ ዓመት ዋስትና መስጠት አለባቸዉ::

  16. አሸናፊዉ ተጫራቾች ዉል ከመፈፀማቸዉ በፊት የእቃዉ ናሙና / sample/ ማቅረብ አለባቸዉ::

  17. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ::

  18. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 03 44 41 65 70 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ:;