Mesfin Industrial Engineering PLC

የጨረታ ማስታወቂያ

ባንያችን መስፍን ኢንዳስትሪያል ኢንጂነሪንግ ኃላ.የተወየግል ኩባንያ (FSWEI ኢንድስትሪ) ከታች በሰንጠረዡ የተፃፈው በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች እንድትሳተፉ ኩባንያችን ይጋብዛል::

ተ.ቁየዕቃው ዓይነት ዝርዝርመለኪያብዛትማብራርያ
01Rim Wheel Disk 8.5x20pieces130

የጨረታ መስፈርት

1. ተጫራቾች በዘርፉ የ2017 ዓ/ም የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የወሩ ቫት ማሳወቅያ ፎቶ ኮፒ በማያያዝ ከጨረታው ዝርዝር (ሰነድ)ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል::

2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የወሩ ቫት ማሳወቅያ ፎቶ ኮፒ የማይመለስ እና ኦርጅናል የሚመለስ በመያዝ የጨረታ ሰነድ ከቀን ከ 01/04/2025 እ.ኤ.አ ጀምሮ እስከ 15/04/2025 እ.ኤአ መቐለ ላጪ ቅርንጫፍ FSWEI ኢንድስትሪ በስራ ሰኣት መወሰድ ይኖርባቸዋል::

3. ጨረታው 15/04/2025 እ.ኤ.አ ከቀኑ 8:00 ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ከሰኣት 8:30 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት መቐለ ዋና መስርያ ቤት በሚገኝ ላጪ FSWEI ኢንድስትሪ ሳፕላይ ቢሮ የሚከፈት ሲሆን ሰነዳቸው የተሟላ ከሆነ ባይገኙም የጨረታ ሰነዱ ይከፈታል::

4. አዲስ አበባ ለሚገኙ ተጫራቾች መቐለ ላጪ መስርያ ቤት በሚገኝ FSWEI ኢንድስትሪ ሳፕላይ ቢሮ የጨረታ ሳንዱቅ ማስገባት ይኖርባቸዋል::

5. ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ቫት(VAT) ጨምሮ መሆኑና አለመሆኑን በግልፅ መጠቀስ አለበት:: ይህ ካልሆነ ግን ያስገቡት ዋጋ ቫት እንደሚያካትት ተቆጥሮ ይወሰዳል::

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ ) ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በታሸገ ፖስታ ከጨረታው ጋር ማስገባት አለባቸው::በፖስታ ያልታሸገ ሲፒኦ ተቀባይነት የለውም::

7. አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተነገራቸው ቀን ጀምሮ በ 5 ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋ ቫት ጨምሮ 10% የውል ማስከበርያ የባንክ ዋስትና (Unconditional bank guarantee) በማሰራት

8. አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን አሸንፈው ውል ካሰሩበት ቀን ጀምሮ በ 05 ቀናት ውስጥ እቃው ማስረከብ አለባቸው::ይህ ካልሆነ ግን ለውል ማስከበርያ ያስያዙት ብር ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ድርጅቱ ሌላ አማራጭ ይወስዳል::

9. ተጫራቾች በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ተመስርተው ዋጋ ማስገባት አይፈቀድም::

10. ተጫራቾች ይህን ጨረታ ካሸነፉ ለሌላ ሶስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት አይችሉም::

11. ተጫራቾች ተጫርተው ያሸነፉት እቃ መቐለ ዋና መስርያ ቤት ድረስ መጥተው ማስረከብ አለባቸው:: ክፍያ በተመለከተ ያቀረቡት እቃ ድርጅታችን ጥራት ቁጥጥር ባለሙያ ተፈትሾ ተቀባይነት ካገኘ በኃላ የሚፈፀም ይሆናል::

12. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::

ለበለጠ መረጃ

መቐለ

ስልክ-+251914702481

ፋክስ- +251-344406225

አዲስ-አበባ

ስልክ-+251-914726541

ፋክስ-+251-114709636