በአክሱም ከተማ የሚገኘውን የኮርፖሬሽን ህንፃ ለማከራየት
የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢ.ግ.ስ.ኮ/ብ/ግጨ /001/2017
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው መስፈርት መሠረት ተጫራቾችን አወዳድሮ በአክሱም ከተማ የሚገኘውን ህንፃ ለቢሮ አገልግሎት ለማከራየት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ የመንግስትም ሆነ የግል ድርጅቶች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ የዘመኑን ግብር ለመክፈላችሁ ማስረጃ፡ የቫት ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ የምዝገባ ሠርትፊኬት (TIN) እንዲሁም ከገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ, ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አቦ ፋፋ የምግብ አክሲዮን ማህበርና ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ መካከል 200 ሜትር ገባ ብሎ የኮርፖራሽኑ ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 110 እንዲሁም አክሱም ከተማ ቀበሌ 03 ፀሐይ በርኪ እንዳይ እጠን ከአንበሳ ባንክ ጎን ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ:: ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ብቻ በሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ (unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል:: የጨረታው ዋጋ ለ60 ቀናት የፀና ይሆናል፡፡ ጨረታው የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ የካቲት 25/2017 ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ የቴክኒካል ጨረታ ስነድ የመክፈቻ ስነሥርዓት ይከናወናል፡፡ ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
ስልክ ቁጥር፡-011470-90-95/0114-42 3608-0114-42 1312 አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን አክሱም ቅ/ጽ/ቤት
ስልክ ቁጥር፡- 09 34 09 3969