ትራንስ ኢትዮዽያ ሃ/የ/የግ/ማሕበር የተለያዩ የከባድ መኪና መለዋወጫ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ አወዳድሮ ለመግዛት ስለፈለገ በዘርፉ የተሰማራቹ አቅራቢዎች ከዚህ በታች የተገለፁ ነጥቦች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ዉ እንድትሳተፉ እንጠይቃለን።

1. ተጫራቶች በተጠቀሰው ዘርፍ የ2016 ዓ/ም የታደስ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ አለባቸው የ2016 ዓ/ም ንግድ ፍቃድ ያላሳደሰ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል።

2. ተጫራቶች የሚያቀርቡት ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው፤ ይህ ካልተገለፀ የቀረበው ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ (Vat) እንዳካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።

3. ተጫራቶች የሚያቀርቡት ሰነድ ስርዝ ድልዝ ያለበት መሆን የለበትም። ስርዝ ድልዝ ያለበት ሰነድ ያቀረበ ተጫራች ከውድድሩ ውጭ ይሆናል።

4. ተጫራቶች ዋጋ መሙላት ያለባቸው ድርጅታችን በሰጣቸው ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ሰነድ ብቻ መሆን አለበት ከዚያ ውጭ በራሳቸው ፕሮፎርማ ዋጋ የሞሉ ተራቶች ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ።

5. ተጫራቶች ነጠላ ዋጋና ድምር ዋጋ በጥንቃቄ መሙላት ኣለባቸው። ነጠላ ዋጋ ከተጠየቀው የዕቃ ብዛት (Quantity) ተባዝቶ ከሚመጣ ድምር ዋጋ ልዩነት ከተፈጠረ ነጠላ ዋጋው ትክክለኛ ተደርጎ ይወሰዳል።

6. ተጫራቶች ለጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ማስከበርያ (Bid Bond) ባቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% በትራንስ ኢ/ያ ሓ/የተ/የግ/ማሕበር ስም የተዘጋጀ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው። ጠቅላላ ዋጋ ማለት ያቀረቡት የሁሉም ዕቃዎች ወይም የሁሉም ሞዴሎች ድምር ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ (Vat) ጨምሮ ማለት ነውየሚቀርብ ሲፒኦ ለብቻው ታሽጎ መቅረብ ኣለበት። ሲፒኦ ያላቀረበ ወይም በተጠቀሰው መጠን መስረት ያላስያዘ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል።

7. አሸናፊ የሆነ ተጫራች ላሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ (ተጫማሪ እሴት ታክስ ጨምሮ) ውል ማስከበርያ (Performance Bond) 10% ማስያዝ ኣለበት።

8. ተጫራቶች ፋይናንሻል ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ሰነድ በመቐለ በዳይሬክተር ግዢና የኣቅራቢዎች ትስስር ቢሮ እንዲሁም በኣዲስ ኣበባ ሳሪስ ኣካባቢ በሚኘኘው ላይዘን ኦፊስ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል መውሰድ ኣለባቸው።

9. ተጫራቶች አሸናፊ መሆናቸው ከተገጸለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀን ውስጥ ውል ማሰር ኣለባቸው።

10. አሸናፊ የሆኑ ተጫራቶች በአዲስ አበባ የተወዳደሩ ወይም በአዲስ አበባ ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ሰነድ ያስገቡ አዲስ አበባ በሚገኘው ላይዘን ኦፊስ በመቐለ የተወዳደሩ ደግሞ መቐለ በሚገኘው ዋና ቢሮ ያሸነፉት ዕቃ ማቅረብ ኣለባቸው።

11. ተጫራቶች የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ሰነድ በታሸገ ፖስታ እስከ ሕዳር 29/2016 ዓ/ም ጠዋት ሰዓት‍‍‍‍‌‍‌‍‌‌‌‍‍‍‌‍ 3:30 በመቐለ በዳይሬክተር ግዢና የአቅራቢዎች ትስስር ቢሮና አዲስ አበባ ሳሪስ አካባቢ በሚገኘው ላይዘን ኦፊስ በተዘጋጀ የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ሳጥን ፋይናንሻል ፕሮፖዛል ኦርጅናልና ፎቶኮፒ ለየብቻ ማቅረብ አለባቸው።

12. ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ው ህዳር 29/2016 ዓ/ም ጠዋት 3:30 ሰኣት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ጠዋት 4:00 ሰአት በመቐለና በአዲስ አበባ ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

13. የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ሰነድ በተቀመጠው የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ምልክታ መሰረት የተሟላ ከሆነ ተጫራቶች ባይገኙም ይከፈታል።

14. ድርጅታችን ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ውሎ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

15. ለተጨማሪ ማብራርያ ወይም ግልፅ ያልሆነላቸው ሃሳብ ተጫራቶች በኣካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 0914 00 77 32/0912 23 07 03 በስራ ሰዓት ደውላቹ መጠየቅ ትችላላቹ።