https://tenders.milkta.com/am/tenders/display/16999
የመቐለ እቅድና ፋይናንሰ ፅፈት ቤት በከተማችን በልማታዊ ሴፍትኔት ባጀት በመጠቀም ለሚሰሩ የተለያዩ ፕሮጀክቶች የሚዉል የተለያዩ የሼድ (SMALL METAL SHADES FOR EY HOOD_BENEFICIARIES) በሾፒንግ ፕራፎር ኣወዳደሮ ለማሰራት ስለሚፈልግ
  • የተለቀቀበት ቀን: ረቡዕ ሚያዝያ 8, 2017 ( ከ 11 ወር)
  • መዝግያ ቀን: ሓሙስ ሚያዝያ 16, 2017 04:00 ጥዋት (ተዘጋ)
  • የጨረታ ማስከበርያ ዋጋ:150,000
  • ቦታ:መቐለ
  • የጨረታ ደኩመንት ዋጋ:300.00
  • ጨረታ ሚከፈትበት ቀንና ሰዓት: ሓሙስ ሚያዝያ 16, 2017 04:30 ጥዋት
  • ምድብ: ጠቅላላ ስራሕቲ ኣገልግሎት/ ሰራሕቲ ሓፂነ መፂን/

የፕሮፎርማ ማስታወቅያ (Shopping)

የመቐለ እቅድና ፋይናንሰ ፅፈት ቤት በከተማችን በልማታዊ ሴፍትኔት ባጀት በመጠቀም ለሚሰሩ የተለያዩ ፕሮጀክቶች የሚዉል የተለያዩ የሼድ (SMALL METAL SHADES FOR EY HOOD_BENEFICIARIES) በሾፒንግ ፕራፎር ኣወዳደሮ ለማሰራት ስለሚፈልግ በዚ ጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉና ከታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች የምታማሉ ህጋዊ ተጫራቶች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

CONTRACT /BID/NO ET-TIGRAY-MEKELLE-432017-CW-RFQ

ተፈላጊ መስፈርቶች

1/ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 300.00 ብር በመክፈል ከመቐለ እቅድና ፋይናንሰ ፅ/ፈት ኣግኣዚ ኦፕሬሽን ህንፃ በሚገኝዉ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 034 መግዛት ይችላሉ።

2/ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ስራ ፍቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣ የኣቅራቢነት ምዝገባ ሰርቲፊኬት ፣ የቫት ምዝገባ ሰርቲፊኬት ' የቅርብ ወር ቫት ሪፖርት ፣ ብቃት መረጋገጫ ሴርቲፍኬት ማቅረብ የሚችሉእና የግንባታ ሰራ ዘርፍ የተሰማሩ መሆን ኣለባቸዉ።

3/ የመወዳደሪያ ሀሳቡ ከ 08/08/2017 ዓ/ም እስከ16/08/2017 ዓ/ም ሰአት4:00 ለተጫራቾች ክፍት ሁኖ የሚቆይ ሲሆን በዚህ ቀን 4:00 ተዘግቶ 4:30 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 034 ይከፈታል፡፡

4/ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ብር 150,000 (ኣንድ መቶ ሃምሳ ሺ ብር ብቻ ) በCPO ፣ ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም የባንክ ዋስትና(Unconditional ) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ኣለባቸው :: የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ግዜ አንስቶ ለ33ቀናት ይሆናል ፡፡

5/ የግንባታ ስራ የሚጀመረዉ ትዕዛዝ ከተሰጠበተ ቀን ጀምሮ 45 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡

6/ በግንባታ ስራዉ ጠቅላላ ዋጋውን በቁጥር መፀሃፍ ኣለባቸው ፡፡ የነጠላ ዋጋ (ዩኒትፕራስ) ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ካለ ነጠላ ዋጋው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡

7/ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ፊርማቸው ፣ ቀን እና የድርጅታቸው ማህተም ማስፈር ይገባቸዋል ፡፡

8/ በጨረታዉ መሳተፈ የሚችሉት በግንባታ ስራዉ ቢያንስ ኣንድ እና ከዚያ በላይ ተመሳሳይ ስራ የሰሩ መሆን ኣለባቸዉ፡፡

9/ የክፍያ ሁኔታ በየግንባታዉ ደረጃ እየታየ የሚከፈልበት ሁኔታ ለተጠናቀቀዉ ስራ በባለሙያ በሃላፊ እየተረጋገጠ መክፈል እንዳለበት በስምምነት ላይ ሊደርስ ይችላል፡፡

10/ የመወዳደርያ ሀሳብ ማቅረብያ ቛንቛው ኣማርኛ ነው ፡፡

11/ በግንባታ (ኣገልግሎት) ስራዉ መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች (BOO) ተያይዟል ፡፡

12/ ማንኛውም ተጫራችች ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰአት በፊት የዋጋ ማቅረቢያው ሰነዱን /የመወዳደርያ ሀሳብ / ማስገባት ይኖርበታል ፡፡ ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰአት በኋላ የቀረበ የዋጋ ማቅረብያ ሰነድ /የመወዳደርያ ሀሳብ ተቀባይነት የሌለው ሲሆን ኢንቨሎፑ ሳይክፈት ለተጫራቹ ተመላሽ እንዲሆን ይደረጋል፡፡

13/ መስራቤቱ የተሻለ ኣማራጭ ካገኘ ጨረታዉ (ሾፒንግን) በከፊል(በሙሉ) የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

14/ የመወዳደርያ ሂሳቡ ዋጋ የሚቀርበው በኢትዮጵያ ብር ነው ''

15/ የጨረታ መወዳደሪያው በሚከተለው መሰረት ይሆናል ፡

15.1/በግንባታ ስራዉ ቴክኒካል መስፈርቶቹን ያማሉ መሆናቸው ይረጋገጣል፡፡

15.2/በቀረበው ዋጋ ላይ የሂሳብ ድምር ስህተት ካለ እንዲታረም ይደረጋል ፡፡

15.3/ውድድሩ የሚካሄደውእና ዝቅተኛ ዋጋ ኣቅራቢ የሚለየው በታረመው ዋጋ መሰረት ይሆናል ፡፡

16/ ጨረታው ህጋዊ መስፈርቱን ካማለት ኣቅራቢዎች መካከል ዝቅተኛ ዋጋ ላቀረበው ተጫራች ኣሸናፊ ይደረጋል ::