https://tenders.milkta.com/am/tenders/display/16974
የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 140 ካሬ ሜትር ስፋቱ ያለው ቤትና ቦታ በጨረታ መሸጥ ይፈልጋል
  • የተለቀቀበት ቀን: ሰሉስ ሚያዝያ 7, 2017 ( ከ 11 ወር)
  • መዝግያ ቀን: ረቡዕ ጉንበት 6, 2017 03:00 ጥዋት (ተዘጋ)
  • የጨረታ ማስከበርያ ዋጋ: 25%
  • ቦታ:መቐለ
  • የጨረታ ደኩመንት ዋጋ:
  • ጨረታ ሚከፈትበት ቀንና ሰዓት: ረቡዕ ጉንበት 6, 2017 06:00 ጥዋት
  • ምድብ: ናይ ገዛ/ህንፃ ሓራጅ/

ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

በአፈጻጸም ከሳሽ ፡- ፅላል ዳዕሮ ራስ አገዝ ህብረት ሥራ ማህበር እና በአፈጻጸም ተከሳሾች እነ ንጉስ አብርሃ ኮንስትራክሽን ህንጻ ተቋራጭ በቁጥር 2(ሁለት) ሰዎች በመካከላቸው ባለው የአፈጻጸም ክርክር ጉዳይ በአንደኛ አፈጻጸም ከሳሽ አቶ ንጉስ አብርሃ ገ/ኪዳን ስም የሚታወቅ በአክሱም ከተማ ንግስተ - ሣባ ቀበሌ የሚገኝ በምስራቅ አቶ ገ/ሔር ፤በምእራብ ጉዕሽ መሰለ በሰሜን- ሻለቃ አታክልቲ በደቡብ መንገድ የሚዋሰን ስፋቱ 140 ካሬ ሜትር የሆነ ቤትና ቦታ በጨረታ እንዲሸጥ ስለታዘዘ በመነሻ ዋጋ ብር 5,721,715.54 (አምስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሀያ አንድ ሺህ ሰባት መቶ አስራ አምስት ብር ከ54/100) የሆነ ስለሚጫረት ለመጫረት የምትፈልጉ በቀን06/9/20/17 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 5፡00 ሰዓት ረፋድ ድረስ ባለው ጊዜ በቤትና ቦታው ተገኝታችሁ እንድትጫረቱ፤ ጨረታ ያሸነፈ ቅድሚያ 25% ማስያዝ የሚችል ቀሪውን ደግሞ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ የሚያደርግ መሆኑን እንዲያውቁ የጨረታው ውጤት ደግሞ በቀን 7/9/2017 3፡00 ሰዓት ወደ ትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍትሐብሔር ችሎት የሚቀርቡ መሆኑን ፍርድ ቤቱ አዟል።

የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት