https://tenders.milkta.com/am/tenders/display/16892
ኩባንያችን መስፍን ኢንዳስትሪያል ኢንጂነሪንግ ኃላ.የተወየግል ኩባንያ (FSWEI ኢንድስትሪ) ከታች በሰንጠረዡ የተፃፈው ለSteel Structure ስራዎች የሚሆኑበግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ
  • የተለቀቀበት ቀን: ረቡዕ መጋቢት 24, 2017 ( ከ 11 ወር)
  • መዝግያ ቀን: ሰሉስ ሚያዝያ 7, 2017 04:30 ጥዋት (ተዘጋ)
  • የጨረታ ማስከበርያ ዋጋ:100,000.00
  • ቦታ:መቐለ
  • የጨረታ ደኩመንት ዋጋ:
  • ጨረታ ሚከፈትበት ቀንና ሰዓት: ሰሉስ ሚያዝያ 7, 2017 05:00 ጥዋት
  • ምድብ: ኮንስትራክሽን ጥረ ኣቁሑት/

የጨረታ ማስታወቂያ

ኩባንያችን መስፍን ኢንዳስትሪያል ኢንጂነሪንግ ኃላ.የተወየግል ኩባንያ (FSWEI ኢንድስትሪ) ከታች በሰንጠረዡ የተፃፈው ለSteel Structure ስራዎች የሚሆኑበግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች እንድትሳተፉ ኩባንያችን ይጋብዛል::

ተ.ቁየዕቃው ዓይነት ዝርዝርመለኪያብዛትማብራርያ
01Steel Cable Ø12,Length 800mm Tensil Strength(1770-2160 MPA)Meter6,600
02Round Steel Ø30x6000mm ST-52pieces100
03Round Steel Ø20x6000mm ST-52pieces12
04Nut & Washer Galvanized M24mm For Anchor Boltpieces9,120
05Welding Wire Thickness Ø1.2mmRoll100
06Welding Wire Thickness 04mmRoll140
07Thinner UN 1263Littre1,300
08Abujedid Width 1.5MeterMeter100

የጨረታ መስፈርት

1. ተጫራቾች በዘርፉ የ2017 ዓ/ም የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የወሩ ቫት ማሳወቅያ ፎቶ ኮፒ በማያያዝ ከጨረታው ዝርዝር (ሰነድ) ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል::

2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የወሩ ቫት ማሳወቅያ ፎቶ ኮፒ የማይመለስ እና ኦርጅናል የሚመለስ በመያዝ የጨረታ ሰነድ ከቀን ከ 01/04/2025 እ.ኤ.አ ጀምሮ እስከ 15/04/2025 እ.ኤ.አ መቐለ ላጪ ቅርንጫፍ FSWEI ኢንድስትሪ በስራ ሰኣት መወሰድ ይኖርባቸዋል::

3. ጨረታው 15/04/2025 እ.ኤ.አ ከቀኑ 4:30 ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ከሰኣት 5:00 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት መቐለ ዋና መስርያ ቤት በሚገኝ ላጪ FSWEI ኢንድስትሪ ሳፕላይ ቢሮ የሚከፈት ሲሆን ሰነዳቸው የተሟላ ከሆነ ባይገኙም የጨረታ ሰነዱ ይከፈታል::

4. አዲስ አበባ ለሚገኙ ተጫራቾች መቐለ ላጪ መስርያ ቤት በሚገኝ FSWEI ኢንድስትሪ ሳፕላይ ቢሮ የጨረታ ሳንዱቅ ማስገባት ይኖርባቸዋል::

5. ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ቫት(VAT) ጨምሮ አለመሆኑን በግልፅ መጠቀስ አለበት:: ይህ ካልሆነ ግን ያስገቡት ዋጋ ቫት እንደሚያካትት ተቆጥሮ ይወሰዳል::

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ ) ብር 100,000.00 (መቶ ሺህ ብር) በታሸገ ፖስታ ከጨረታው ጋር ማስገባት አለባቸው::በፖስታ ያልታሽገ ሲፒኦ ተቀባይነት የለውም::

7. አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተነገራቸው ቀን ጀምሮ በ 5 ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋ ቫት ጨምሮ 10% የውል ማስከበርያ የባንክ ዋስትና (Unconditional bank guarantee) በማሰራት ከኩባንያችን ጋር ውል መፈራረም አለባቸው:: ይህ ካልሆነ ግን ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዙት ብር ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ድርጅቱ ሌላ አማራጭ ይወስዳል::

8. አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን አሸንፈው ውል ካሰሩበት ቀን ጀምሮ በ 05 ቀናት ውስጥ እቃው ማስረከብ አለባቸው::ይህ ካልሆነ ግን ለውል ማስከበርያ ያስያዙት ብር ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ድርጅቱ ሌላ አማራጭ ይወስዳል::

9. ተጫራቾች በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ተመስርተው ዋጋ ማስገባት አይፈቀድም::

10. ተጫራቾች ይህን ጨረታ ካሸነፉ ለሌላ ሶስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት አይችሉም::

11. ተጫራቾች ተርተው ያሸነፉት እቃ መቐለ ዋና መስርያ ቤት ድረስ መጥተው ማስረከብ አለባቸው:: ክፍያ በተመለከተ ያቀረቡት እቃ ድርጅታችን ጥራት ቁጥጥር ባለሙያ ተፈትሾ ተቀባይነት ካገኘ በኃላ የሚፈፀም ይሆናል::

12. ኩባንያው የተሻለ ማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::

ለበለጠ መረጃ

አዲስ-አበባ ስልክ-+251-914726541

ፋክስ-+251-114709636