በዚህም መሰረት ሎት 1 እስከ ሎት 6 ለተጠቀሱት በዘርፉ የተሰማሩ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት፣የቫት ተጠቃሚ ሰርተፊኬት እና የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸውን እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መመሪያ እና ዝርዝር ሰነድ የያዘ ከሎት 1 እስከ ሎት 6 ለአንዱ የማይመለስ 100.00/ አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ሽራሮ በሚገኘው የ23ኛ አሉላ ክ/ጦር ጠቅላይ መምሪያ ግዥ ዴስክ ቢሮ በመምጣት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የጨረታ ሰነድ በመግዛት በቢሮው ወደ ተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ጨረታው ጥቅምት 23/02/2013 ዓ/ም ከጠዋቱ 04:00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 04:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
በአገር መከላከያ ሚኒስቴር በሰሜን ዕዝ
የ23ኛ ክ/ጦር ጠ/መምሪያ
መመለስ