ጨረታ መለያ ቁጥር
BOARD/LESDP/NCB/POAE-26/2011
የትግራይ ክልል ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ከእንስሳት እና ዓሣ ሀብት ሴክተር ልማት /LFSDP/ ፕሮጀክት በተገኘው በጀት
- የእርሻ መገልገያ ፤ መሳሪያ/ ቾፐር/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ እየጋበዝን፤ የተዘጋጀው የጨረታ ዶክሜንት ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ የኢትዮጵያ ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቀሌ ቅርንጫፍ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000012030839 Ministry of Agriculture . Office በሚል ገቢ በማድረግ ከ2/10/2011 ዓ.ም ጀምሮ ሕጋዊ የንግድ ፈቃዳችሁን በመያዝ ከቢሯችን የዕቃ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 በሥራ ሰዓት እየመጣችሁ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ በጨረታው ለመሳተፍ ቀጥለው የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ያስፈልጋል፦
- የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የVAT ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin) እና ቫት (VAT) ዲክለር የተደረገበት ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ኣብሮ መቅረብ አለበት፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በጨረታ ዶክመንቱ ላይ የተጠቀሰው መጠን ገንዘብ በCPO አሠርተው ጨረታው ከመከፈቱ በፊት አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ 2/11/2011 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሯችን ቢሮ ቁጥር 12 የግዥ ክፍል ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ መመሪያውን በጥንቃቄ አይተው መወዳደር አለባቸው::
- ቢሯችን የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥሮች:- 034 440 3663/
034 440 4346 ወይም
በፋክስ ቁጥር፡- 034 440 9971 መጠየቅ ይቻላል።
የትግራይ ክልል ግብርና ገጠር
ልማት ቢሮ