ኢማጂን ዋን ዴይ ኢንተርናሽናል ኦርጋናይዜሽን

ኢማጅን ዋን ዴይ ኢንተርናሽናል ኦርጋናይዜሽን /Imagine 1day/ በተባለ መ/ታዊ ያልሆነ የውጭ በጎ ኣድራጎት ድርጅት ትግራይ ፣ በኦሮሚያ እና በደቡብ ክልል በትምህርት ጥራት ማሻሻል ሰራ ላይ አና በላይቪሊ ሁድ ዴቬሎፕመንት // የበኩሉን ኣስተዋፀኦ እየሰጠ ይገኛል፡፡

 በኣሁኑ ጊዜም ድርጅታችን በትግራይ ክልል በክልተ ኣውላዕሎ ወረዳ ገማድ ቀበሌ በደረባ ወሃቢት ሕ/ሰብ ለኑሮ ማሻሻያ እና ድህነት ቅነሳ የሚያግዙ የተሻለ ዝርያ ያለቸው 2500 ደሮዎች እና 50 ኩንታል የደሮ ቀለብ ከመድሃኒት ጋር ኣቅራቢያዎች በጨረታ አወዳድሮ ይፈልጋል

1 ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

2 የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ስፒኦ ለ30 ቀናት የሚቆይ ከሚያቀርቡት ዋጋ ላይ 2% ጨረታዉ ከመከፈቱ በፊት ለብቻ በታሸገ ፖስታ ኢንቨሎፕ ማስያዝ የሚችሉ፤

3 ስለጨረታዉ የሚገልፀዉን ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00 እና የታደሰ ንግድ ፈቃዳቸዉን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤

4 ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በትግራይ ክልል በመቐለ ከተማ 14 ቀበሌ ሃፀይ ዩሃንስ ሆቴል በስተጀርባ ፋና ህንፃ 4ኛ ፎቅ ካለዉ የድርጅቱ ፅሕፈት ቤት ገዝተዉ መዉሰድ ይችላሉ፡፡

7 የሚወዳደሩበት ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ሰኔ 06 ቀን 2011 ዓም ከ8:00 ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ላይ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

8 ተጫራቾች ሁሉ ከዚህ ደብዳቤ ጋር የተያያዘዉን ዝርዝር ዕቃዎች ዋጋ በሞሞላት ጨረታዉ 06/10/2011ዓ/ም 8:00 ሰዓት ላይ ራሳቸዉ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት 14 ቀበሌ ሃፀይ ዩሃንስ ሆቴል በስተጀርባ ፋና ህንፃ 4ኛ ፎቅ ካለዉ የድርጅቱ ፅሕፈት ቤት ይከፈታል፡፡

9 ድርጅቱ የተሻለ ኣማራጭ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ

ኣድራሻ : ኢማጅን ዋን ዴይ +251344404933