የጨረታ መስፈርት

1 ተጫራቾች ቫት ተመዝጋቢ እና የ2010 ዓ/ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የግብር መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ መሆን ኣለባቸው ።

2 ተጫራቶች የማይመለስ ኣንድ የታደሰ ንግደ ፍቃድና የግብር ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ በማያያዝ የጨረታ ዋጋ በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 18/01/2011ዓ/ም 6:00 ሰዓት መቐለ ድህረ ሽያጭ ኣገልግሎት ሳፕላይ መምርያ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

3 የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50 (ኣምሳ ብር) በመክፈል ከመቐለ ድህረ ሽያጭ ኣገልገሎት ሳፕላይ መምሪያ ዘወትር በስራ ሰዓት ከ 14/01/2011 ዓ/ም ጥዋት 2:00 ጀምሮ እስከ 18/01/2011ዓ/ም ከቀኑ 8:00 መውስድ ይቻላል።

4 ተጫራቾች የጨረታ ማስከበረያ ሲፒኦ ብር 15000.00(ኣስራ ኣምስት ሺ ብር) በስም በታሸገ ፖስታ ማስገባት ኣለባቸው።በፖስታ ያልተሸገ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ተቀባይነት የለውም።

5 ጨረታ ሰነዱን ጨረታ ማስከብርያ ዋጋ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ ማስገባት ኣለባቸው።

6 ተጫራቾች ይህን ጨረታ ካሸነፉ ለሌላ ሦስተኛ ወገን ኣሳልፎ መስጠት ኣይችሉም።

7 ጨረታው 18/01/2011 ዓ/ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ዕለት 8:30 ታጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት መቐለ ድህረ ሽያጭ ኣገልግሎት ሳፕላይ መምሪያ የሚከፈት ሲሆን ሰነዳቸው የተሟላ ከሆነ ባይገኙም የጨረታ ሰነዱ ይከፈታል። ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ቫት ጨምሮ መሆኑና ኣለመሆኑን በግልፅ መቀመጥ ኣለበት።

ይህ ካልሆነ ግን ያስገቡት ዋጋ ቫት እንደሚያካትት ተቆጥሮ ይወስዳል።

8 ያስገቡት ዋጋ ስርዝ ድልዝ ከሆነ ተቀበይነት የለውም።

9 በጨረታው ያሸነፈ ለ 3 ወር ውል እንዲያስር ያደርጋል።