የፕሮፎርማ ግዢ ማሰታወቅያ
መስሪያ ቤታችን ከዚህ ደብዳቤ ጋር ኣባሪ በተደረገው ሠንጠረዥ ውስጥ የተጠቀሱት የቢሮ መግዛት ሰለሚፈልግ የመወዳደሪያ ሀሳብ እንድታቀርቡ ይጋብዛል:: መስሪያ ቤታችን ግዢውን የሚፈፅመው በጥራትም ሆነ በዋጋ ብቁ መሆናቸውን አረጋግጦ የመረጣቸውን ይሆናል።
1. የተፈላጊ ዕቃዎች ዝርዝር ኣባሪ በተደረገው ሠንጠረዥ ላይ ተመልክተዋል።
2. ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ለመሳተፍ የሚያስችላቹ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TI/፣ ለሻት
ተመዝጋቢዎች የሻት ምዝገባ ሰርቲፊኬትና ፣ በመንግስት ግዢ ለመሳተፍ የተሰጠ ፍቃድ ማሰረጃዎች ፎቶ ኮፒ መያያዝ አለበት"
3. ማንኛውም በውድድሩ የሚሳተፉ አቅራቢዎች ከገቢዎች መስራቤት የተፈቀደ ተከታታይ ቁጥር ያለው ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል ብቻ ይሆናሉ፡ ብድርጅታቸው ስም ተከታታይ ቁጥር ያለው ደረሰኝ ማቅረብ የማይችል ተወዳዳሪ TOT / VAT)ምዝገባ ሰርቲፊኬት ኮፒ
ከመወዳደርያ ሰነዱ ያላቀረበ ተሳታፊ በቅድመ መጣርያ ውድድሩ ውድቅ ይሆናል፡፡
4. የመወዳደርያ ሃሳቡ በታሸገ ኢንቨሎፕ ሆኖ እስከ 05/03/2018 ዓ/ም ጥዋት 4፡00 ሰዓት ለቢሯችን የግዢ ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 መድረስ አለበት ፕሮፎርማው/የመወዳደርያ ሃሳቡ/ በ 05/03/2018 ዓ/ም ጥዋት 4፡00 ተዝግቶ ወድያውኑ ይከፈታል።
5. አሸናፊ አቅራቢ የሚለየው ለእያንዳንዱ ዕቃ ያቀረበው ( Item by Item) ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ መሰረት ይሆናል።
6. የእቃው ማስረከብያ ቦታ በቢሯችን በሚገኘው ንብረት ክፍል ሆኖ ማስረከብያ ግዜው ግዢው ከታዘዘበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ይሆናል።
7. የፕሮፎርማው ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ጊዜ አንስቶ ለ 15 ቀናት ይሆናል።
8. አቅራቢዎች በእያንዳንዱ የዕቃ ዝርዝር ማቅረብያ ሰንጠረዥ ውስጥ የዕቃው ዓይነትና ብዛት፣ነጠላ ዋጋ፣እና ጠቅላላ ዋጋውን መሙላት እንዲሁም ቀን ፣ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም ማሰፈር ይገባቸዋል የመወዳደርያ ሂሳቡ ዋጋ የሚቀርበው በኢትዮዽያ ብር ይሆናል
9. ለአሸናፊ ተወዳዳሪ ዕቃውን ሙሉ ለሙሉ በውሉ መሰረት አጠናቆ ማስገባቱና ጥራቱ ከተረጋገጠ በኃላ በሰባት ቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያ ይከፈለዋል።
10. ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ታክስን የሚያካትትና የማያካትት መሆኑ መግለፅ አለባቸው።
ታክስ በትክክል ካልተገለፀ የቀረበው ዋጋ ታክስ እንዳካተተ ተቆጥሮ ውድድሩ ይካሄዳል።
11. ግዢ ፈፃሚው መስራቤት ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ከያንዳንዱ የእቃዎች ብዛት እስከ 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት)ጨምሮ ወይም
ቀንሶ ማዘዝ ይችላል።
12. ማንኛውም ተሳታፊ ከፕሮፎርማ መዝግያ ቀንና ሰዓት በፊት በኢንቨሎፕ በማሸግ ኦርጅናል ሰነዶችን /የመወዳደርያ ሃሳብ/ ማቅረብ ይኖርበታል " ከፕሮፎርማው መዝግያ ቀንና ሰዓት ሰዓት በኃላ የቀረበ ሰነድ /የማወዳደርያ ሃሳብ/ ተቀባይነት የሌለው ሲሆን አንሸሎፑ ሳይከፈት ለተወዳዳሪው ተመላሽ ይሆናል።
13. የቴክኒክ መስፈርቱን/ በ ተጠየቀው ዝርዝር መግላጫ/Specification መሰረት/ ካሟሉት አቅራቢዎች መካከል የተስተካከለ ዝቅተኛ ዋጋ ላቀረበው ተጫራች አሸናፊ ይደረጋል።
14. መስርያ ቤታችን ፕሮፎርማው በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
| ተ.ቁ | የዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር | መግለጫ/እስፔሲፊኬ | መለኪያ | ብዛት | Unit price የአንድ ዋጋ በብር | Total Price ጠቕላላ ዋጋ | ማብራርያ |
|---|---|---|---|---|---|---|---|
| 1 | Air Freshener Spray | 300 ml Elegant | PCS | 16 | |||
| 2 | Tissue Paper for office | 180 pcs per box | PCS | 600 | |||
| 3 | Detergent(Omo ) | 1 kg Sunlight | PCS | 140 | |||
| 4 | Hand wash Soap liquid | 500ml | PCS | 161 | |||
| 5 | Hand Sanitizer | 236ml | PCS | 32 |