የጨረታ ማስታወቂያ
በአፈጻጸም ከሳሽ ዕላል ዳዕሮ ራስ አገዝ ህብረት ማህበር እና በአፈጻጸም ተከሳሾች እነ ንጉሰ አብርሃ ኮንስትራክሽን ህንጻ ተቋራጭ በቁጥር 2 (ሁለት) ሰዎች በመካከላቸው ባለው የአፈጻጸም የሚል ክርክር ጉዳይ በአንደኛ አፈጻጸም ተከሳሽ አቶ ንጉሰ አብርሃ ገ/ኪዳን ስም የሚታወቅ በአክሱም ከተማ የሚገኝ በምስራቅ ገ/ሔር፣ በምእራብ ጉዕሽ መሰለ፣ በሰሜን ሻለቃ አታክልቲ፣ በደቡብ መንገድ የሚዋስን ስፋቱ 110 ካሬ ሜትር የሆነ ቤትና ቦታ በጨረታ እንዲሸጥ ስለታዘዘ በመነሻ ዋጋ ብር 5,721,715.54 (አምስት ሚልዮን ሰባት መቶ ሃያ አንድ ሺህ ሰባት መቶ አስራ አምስት ብር ከ 54/100) ሆኖ ስለሚጫረት ለመጫረት የምትፈልጉ በቀን 09/7/2017 ዓ.ም ከ3:00 ሰዓት እስከ 5:00 ሰዓት ረፋድ ድረስ ባለው ጊዜ በቤትና ቦታው ዘንዳ ተግኝታችሁ እንድትጫረቱ፤ ጨረታ ያሸነፈ ቅድሚያ 25% ማስያዝ የሚችል፤ ቀሪውን ደግሞ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ የሚያደርግ መሆኑን እንዲያውቅ፤ የጨረታው ውጤት ደግሞ በቀን 10/7/2017 ዓ.ም 4:00 ሰዓት ወደ ትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍትሐብሄር ችሎት የሚቀርብ መሆኑን ፍርድ ቤቱ አዟል፡፡
የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት