የጨረታ ማስታወቂያ
አፈ/ከሳሽ፡- ሞሞና መቐለ ዩኒቨርሲቲ የራስ አገዝ የመኖርያ ቤቶች ሕ/ሰ/ማህበር እና አፈ/ተከሳሽ፡- ደጀን ባህታ ኮንትራክተር መካከል ባለው የአፈፃፀም ክርክር ጉዳይ በአፈ/ተከሳሽ ደጀን ባህታ ኮንትራክተር ስም የሚታወቅ ታርጋ ቁጥር ኢት-54172 የሆነ ገልባጭ መኪና በግልፅ ጨረታ እንዲሸጥ ስለታዘዘ የመነሻ ዋጋ ብር 1,693,310.39 (አንድ ሚልዮን ስድስት መቶ ዘጠና ሶስት ሺ ሶስት መቶ አስር 39/100 ብር) ስለሆነ ለመጫረት የምትፈልጉ ተጫራቾች መኪናው በገሬ ጋራጅ ስለሚገኝ በ 23/04/2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00–5፡00 በቦታው ተገኝታችሁ እንድትጫረቱ የጨረታው ውጤት ደግሞ በተጠቀሰው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት እንዲቀርብ የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍትሀብሔር ችሎት አዟል።
የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍትሀብሔር ችሎት