የጨረታ ማስታወቂያ

ኩባንያችን መስፍን ኢንዳስትሪያል ኢንጂነሪንግ ኃላ.የተወየግል ኩባንያ (FSWEI ኢንድስትሪ) ከታች በሰንጠረዡ የተፃፈው የቀለም ኣይነቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች እንድትሳተፉ ኩባንያችን ይጋብዛል::

ተ.ቁየዕቃው ዓይነት ዝርዝርመለኪያብዛትማብራርያ
01Paint, antirust RedLittre3,976.00
02Paint,antirust Gray 420Littre3,976.00
03Round Steel O 30x6000mm, st-37pieces230St-37
04Drill Bit Tapper Shanker Ø 14mmpieces30

የጨረታ መስፈርት

1. ተጫራቾች በዘርፉ የ2016 ዓ/ም የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው : የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ : የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የወሩ ቫት ማሳወቅያ ፎቶ ኮፒ በማያያዝ ከጨረታው ዝርዝር (ሰነድ)ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል::

2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የወሩ ቫት ማሳወቅያ ፎቶ ኮፒ የማይመለስ እና ኦርጅናል የሚመለስ በመያዝ የጨረታ ሰነድ ከቀን ከ 12/12/2024 እ.ኤ.አ ጀምሮ እስከ 27/12/2024 እ.ኤ.አ መቐለ ላጪ ቅርንጫፍ FSWEI ኢንድስትሪ በስራ ሰኣት መወሰድ ይኖርባቸዋል::

3. ጨረታው 27/12/2024 እ.ኤ.አ ከቀኑ 8:00 ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ከሰኣት 8:30 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት መቐለ ዋና መስርያ ቤት በሚገኝ FSWEI ኢንድስትሪ ሳፕላይ ቢሮ የሚከፈት ሲሆን ሰነዳቸው የተሟላ ከሆነ ባይገኙም የጨረታ ሰነዱ ይከፈታል::

አዲስ አበባ ለሚገኙ ተጫራቾች የሚያስገቡት የጨረታ ሰነድ መቐለ ዋና መስርያ ቤት በሚገኝ ላጪ ቅርንጫፍ FSWED ኢንድስትሪ ሳፕላይ ቢሮ መሆን አለበት::

5. ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ቫት(VAT) ጨምሮ መሆኑና አለመሆኑን በግልፅ መጠቀስ አለበት:: ይህ ካልሆነ ግን ያስገቡት ዋጋ ቫት እንደሚያካትት ተቆጥሮ ይወሰዳል::

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ ) ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)

በታሸገ ፖስታ ከጨረታው ጋር ማስገባት አለባቸው::በፖስታ ያልታሸገ ሲፒኦ ተቀባይነት የለውም::

7. አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተነገራቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋ ቫት ጨምሮ 10% የውል ማስከበርያ የባንክ ዋስትና (Unconditional bank guarantee) በማሰራት ከኩባንያችን ጋር ውል መፈራረም አለባቸው:: ይህ ካልሆነ ግን ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዙት ብር ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ድርጅቱ ሌላ አማራጭ ይወስዳል::

8. አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን አሸንፈው ውል ካሰሩበት ቀን ጀምሮ በ20 ቀናት ውስጥ እቃው ማስረከብ አለባቸው::ይህ ካልሆነ ግን ለውል ማስከበርያ ያስያዙት ብር ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ድርጅቱ ሌላ አማራጭ ይወስዳል::

9. ተጫራቾች በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ተመስርተው ዋጋ ማስገባት አይፈቀድም::

10. ተጫራቾች ይህን ጨረታ ካሸነፉ ለሌላ ሶስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት አይችሉም::

11. ተጫራቾች ተጫርተው ያሸነፉት እቃ መቐለ ዋና መስርያ ቤት ድረስ መጥተው ማስረከብ አለባቸው:: ክፍያ በተመለከተ ያቀረቡት እቃ ድርጅታችን ጥራት ቁጥጥር ባለሙያ ተፈትሾ ተቀባይነት ካገኘ በኃላ በ10 ቀናት ውስጥ የሚፈፀም ይሆናል::

12. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::