የሐራጅ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
በአፈ ከሳሽ ዶ/ር ሃይሉ በላይ ፡ በኣፈ/ ተከሳሽ ወ/ሮ አልማዝ በየነ መካከል ባለው የአፈጻጸም ክርክር ጉዳይ በመቐለ ከተማ ፣ ሰሜን ክ/ከተማ፣ ሰውሒ ንጉስ ቀበሌ ክልል ውስጥ ከመነን ሆቴል ጎን የሚገኝ በካርታ ቁጥር 01/ 1111 በወ/ሮ አልማዝ በየነ ሥም የሚታወቅ በምስራት መንገድ በምእራብ ሃለቃ አይነኩሉ በሰሜን ወ/ማርያም በደቡብ ወ/ሮ ብዙ የሚዋሰን 275.93 ካሬሜትር ውስጥ የሰፈረ ቤትና ቦታ በመነሻ ዋጋ ብር 7,738,478.76 ( ሰባት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰላሳ ስምንት ሺ አራት መቶ ሰባ ስምንት ብር 76/100) በ24/4/2017 ዓ.ም ከ3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 በግልጽ ጨረታ እንዲሸጥ የመቐለ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዟል። ስለዚህ ለመጫረት የምትፈልጉ ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ ካርድ በመያዝ በተገለጸው ቤትና ቦታ ቀንና ሰዓት ተገኝታችሁ ለመጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ጨረታ ያሸነፈ ያሸነፈበትን ዋጋ 25% በሞ/85 ወዲያውኑ በማስያዝ የቀረውን ደግሞ በአስር ቀን ውስጥ የመክፈል ግዴታ ያለበት መሆኑን ፍርድ ቤቱ አሳውቋል።
በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመቐለ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት